NEWS

በጀርመኑ ምክትል ቻንስለርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲግማር ጋብሬል የሚመራ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ጉብኝት እያደረገ ነው

By Admin

May 03, 2017

በጀርመኑ ምክትል ቻንስለርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲግማር ጋብሬል የሚመራ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

ቡድኑ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የገባው ትናንት ምሽት ነው፡፡

በዚሁ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ሲግማር ጋብሬል በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው የሚመክሩ ሲሆን በተጨማሪም ከአፍሪካ አገራት አምባሳደሮችና ከአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ጋር ውይይት ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡