NEWS

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማስፋት እንደምትፈልግ ገለጸች

By Admin

May 12, 2017

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ አጠቃላይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ ማድረግ እንደምትፈልግ ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ  ይህን የገለጹት በበጂንግ ለሚካሄደው አለም አቀፉ “ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ” ፎሮም ላይ ለመሳተፍ  በጂንግ ከገቡት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ“በአዲሱ የአለም የኢኮኖሚ አሰላለፍ፤ ዘመናዊ ዕድገትና ልማትን በማጣመር ፍትሃዊና ዘመናዊ ዕድገትን ለማምጣት ያለመ ነው፡፡

ግንቦት 6 እና 7 በቤጂንግ በሚካሄደው የኢኒሴቲቩ ፎረም ላይ ከአንድ መቶ አስር በላይ አገራትና ከሀያ ስምንት በላይ የአገራት መሪዎች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል።

ኤኒሼቲቩ እ.ኤ.አ እስከ 2050 የአለምን 80 በመቶ ጠቅላላ አገራዊ ምርት አስተዋፅኦ በማበርከት ከሶስት ቢሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህዝቦችም መካከለኛ ገቢ እንዲኖራቸው ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፤ ሺንዋ