CURRENT

አሜሪካ ለግንቦት 20 የድል በዓል የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፈች !!

By Admin

May 27, 2017

የፊታችን እሁድ የሚከበረውን 26ኛውን የግንቦት 20 የድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ሚኒስትሩ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በአሜሪካ ህዝብ ስም ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ ኢትዮጵያውያንን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሞቀ ወዳጅነት እንዳላቸው አንስተዋል።

ለዴሞክራሲ፣ ለኢኮኖሚ ብልፅግና፣ ለሰብዓዊ መብት መጠበቅ እና የህግ የበላይነት መከበር ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመስራት የአሜሪካ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑንም ነው የገለፁት።

አሁን ላይ በዓለም ላይ ያሉ ፈተናዎች የቀረበ ትብብር እና ግልፅ ውይይት የሚፈልጉ ናቸው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲለርሰን፥ ለእነዚህ ፈተናዎች መፍትሄ ለመስጠት ዩናይትድ ስቴትስ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንደምትሰራ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባል እንደመሆኗም አሜሪካ በምክር ቤቱ በጋራ እንደምትሰራ በመልካም ምኞት መግለጫቸው አስታውቀዋል።