አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እየተመዘበረች መሆኑ ተገለጸ
አፍሪካ በየዓመቱ በበሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እንደምትዘረፍ የብሪታኒያ እና የአፍሪካ ባለሙያዎችን ጥናትን ዋቢ በማድረግ ዘጋርዲያን ዘገበ፡፡
እንደ ጥናቱ ከሆነ ከአፍሪካውያን ይልቅ የተቀረው ዓለም ከአፍሪካ ሀብት ተጠቃሚ ነው፡፡
እ.አ.አ በ2015 162 ቢሊዮን ዶላር በእርዳታ እና ብድር አፍሪካ ስትቀበል በተመሳሳይ ዓመት 203 ቢሊዮን ዶላር አህጉሪቱ ተመዝብራለች፡፡
አህጉሪቱ የሚታየው የህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር 68 ቢሊዮን ዶላር በዓመት ይደረሳል፣ ይህም አህጉሪቱ በዓመት ከምታገኘው የ19 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ የበዛ ነው፡፡
የዚህ ሁሉ የገንዘብ ቀውስ ምክንያየቱ ፍትዓዊ የብድር አከፋፈል አለመኖር፣ የውጭ ድርጅቶች የግብር መደበቅ ዝንባሌ እና ሙስና መሆናቸው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
እ.አ.አ በ2015 አፍሪካ 32 ቢሊዮን ዶላር የተበደረች ሲሆን በዛው ዓመት 18 ቢሊዮን ዶላር ለብድር ወለድ ብቻ ከፍላለች፡፡ ይህም የብድር ወለዱ አፍሪካን ምን ያህል እየበዘበዛት እንደሚገኝ ያሳያል ፡፡
በመሆኑም ወደ አፍሪካ የሚገቡ ኢንቨስትመንቶች በግብር ገነት ውስጥ መኖራቸው አስፈላጊ አለመሆኑን ጥናቱ ይመክራል፡፡ ወደ አህጉሪቱ የሚገቡ ብድር እና ድጋፎችም ተልዕኳቸው ሊታወቅ ይገባል እንደ ጥናቱ ማብራሪያ፡፡