Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮዽያን ለአለም የጤናው ዘርፍ ተምሳሌትነት ያበቋትን ዶክተር እንምረጥ

0 1,225

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ትርጉም  ሃብታሙ አክሊሉ /ከስትራንቲክ ድረገጽ/

ያለፉት 25 አመታት በጤናው መስክ በአለም እውነተኛና ወርቃማ ተግባራት የተከናወኑበት እንደነበር የታሪክ ጠበብት ምስክር ሊሰጡት እንደሚችሉ በዘገባው መጀመሪያ ያስነበበው ስትራቲንክ ድረ ገፅ አዳዲስ የዘርፉ እምቅ አቅሞችና ፖለቲካዊ አመራር በአለም አቀፍ ደረጃ ቢሊዮኖች ተጠቃሚ የሆኑበትን ተግባር በመምራቱ ረገድ ከዚህ ቀደም ያልታየ ውጤት ሊያስመዘግቡ መቻላቸውን ፅፏል።እንደ ኤች አይ ቪ፣የሳንባ ነቀርሳና ወባ ያሉ ገዳይ በሽታዎች ላይ ቀጣይነትና ተከታታይነት ያለው ዘመቻ በመክፈት የሰው ልጅ የመሞት መጠን በግማሽ ተቀንሷል፤ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ህፃናትን ከሞት አደጋ ለመታደግ ተችሏል።

በአለም ደሃ ከሚባሉት ሃገራት ተሰልፋለች ተብላ የሚነገርላት ሃገር ኢትዮዽያ የአለም የጤናው ዘርፍ ስኬት ምሳሌ ተደርጋ ተወስዳለች። ሃገሪቷም እኤአ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የህጻናት ሞትን በ70 በመቶ እየቀነሰች ትገኛለች። በተጠቀሰው አመትም በኤች አይቪ አማካይነት ይፈጠር የነበረን ኢንፌክሽን በ90 በመቶ ስትቀንስ በወባ አማካይነት የሚከሰት ሞትን በ75 በመቶ እንዲሁም የቲቢ በሽታ ሞትን በ64 በመቶ መቀነሷን ድረ ገፁ አብራርቷል።እንደ ድረ ገፁ ይህንን ስኬት እጅግ አስገራሚ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ ሃገሪቷ በጦርነት በሚታመሱ ሃገራት መሃከል ተሰይማ ውጤታማ ስራ መስራቷ ነው።

ይህ አስገራሚ ውጤት አንዲሁ የመጣ አለመሆኑን ያብራራው ፅሁፉ የሃገሪቱን የጤና ስርአት በማሻሻል አስገራሚ በሚባል ደረጃ የጤና አጠባበቅ የዲዛይን ለውጥ በማድረግ የመጣ መሆኑን አትቷል።የኢትዮዽያ መንግስት በሃገሪቱ አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት ለመስጠት 40 ሺ ሴቶችን በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን አሰልጥኖ የመቅጠር ተግባር አከናውኗል።

በዚህ ወቅትም አለም የኢትዮዽያን ተሞክሮ የሚጋራበት ዕድል አጋጥሞታል።በነገው ዕለትም ለመጀመሪያ ጊዜ 194ቱም አባል ሃገራት በቀጣይ የአለም የጤና ድርጅትን የሚመሩ ዳይሬክተርን ለመምረጥ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከላይ የተጠቀሱት የኢትዮዽያ የጤና ዘርፍ ስኬቶች ቀያሽ፣የኢትዮዽያን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን የመሩ ከተወዳዳሪ ዕጩዎቹ አንዱ ናቸው።ዶክተሩ ከተመረጡ በአፍሪካው የአለም አቀፉ የጤና ድርጅትን (WHO)ለመምራት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ይሆናሉ።

ጤናን በተመለከተ ያሉ ተጋላጭነቶች ሊቀነሱ ይገባል።በቀድሞ የአሜሪካ የሃብት አስተዳደር ሃላፊ የተዘጋጀውና ‘ዘ ላንሴት ኮሚሽን ኦን ኢንቨስቲንግ ሄልዝ’ በተሰኘው ፅሁፍ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ ትውልድ በአለማችን ሞት አማጭ የሆኑ በሽታዎች ዋነኛ መንስዔዎችን ለመቀነስ የሚያስችል አቅም እንዳላት አስቀምጧል።ስለሆነም አለማችን በጤናው ዘርፍ ትክክለኛ ኢንቨስትመንትና ትክክለኛው የዘርፉ መሪ ያስፈልጋታል።

የፅሁፉ አቅራቢ እኤአ በ2012 ከዶ/ር ቴዎድሮስ ጋር አብሮ የመስራት አጋጣሚውን አስመልከቶ ሲናገር በወቅቱ ዩ ኤስ አሜሪካ፣ህንድና ኢትዮዽያ መከላከል በሚቻሉ በሽታዎች የህፃናትና እናቶች ሞት ይቁም በሚል ርዕስ በትብብር ይሰሩ ነበር።ሃገራቱም ጥሪ አቅርበው ነበር።ዶክተሩ በጊዜው ኤች አይ ቪ ኤድስን፣ቲቢን እና የወባ በሽታን ለመከላከል በተቋቋመው አለምአቀፍ ፈንድን (Global Fund to Fight AIDS, Tuberculosis and Malaria) ጨምሮ ሌሎች ሃላፊነቶች ማለትም የአለም አቀፍ ተቋማት የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ሲሰሩ ማስተዋላቸውን ፅፈዋል።በይበልጥም ዶክተር ቴዎድሮስ ሃገራት ቀጣይነት ያለው የጤና ስርአት እንዲገነቡ እገዛ ሲያደርጉ መመልከታቸውንም አልሸሸጉም።

የጤና ሽፋንን ተቋማዊ ማድረጉ ላይ (በተለይም የአቅም ውስንነት ላለባቸው ሃገራት ) አለማችን ፈታኝ ከሆኑባት ጉዳዮች  ይጠቀሳሉ ያለው ድረ ገፁ በጤና ጥበቃ ሚኒስትርነታቸው ዶክተሩ ያስተዋወቋቸው ማህበረሰብን መሰረት ያደረገውና በዚህ ጊዜ 15 ሚሊዮን ሰዎችን የደረሰው የጤና ኢንሹራንስና በአስር እጥፍ ያደገው የጤና ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ያላቸውን ጠቀሜታ ማየት እንደሚገባ ፅሁፉ አስቀምጧል።

ኢትዮዽያ የአለም አቀፍ የጤና ህጎችን በማስተዋወቁ ረገድ ተባባሪ በመሆንና የበሽታ መቀስቀስ ቅኝትና ሪፖርት ማድረግም ላይ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ተግባራትን አከናውናለች።የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል በሃገሯ እንዲከፈትም አድርጋለች።

አንደ ሌሎቹ ሃገራት ሁሉ ኢትዮዽያም በዘርፉ ያልተሻገረቻቸው ጥቂት ችግሮች አሉባት፤ይሁን እንጂ ሃገሪቷ በማንኛውም መለኪያ በጤናው ዘርፍ አዲሷ የአለም ተምሳሌትነቷን እያስመሰከረች ትገኛለች ያለው መረጃው ለዚህ ስኬት ደግሞ ፈጠራ የታከለበት የዶ/ር ቴዎድሮስ አመራር ሚናው የጎላ እንደሆነ አስረድቷል።ይህ የአመራር ውጤት በተለይ በማደግ ላይ ላሉ ሃገራት እርካታ በሚሆን መልኩ ልንመለከተው ይገባል ሲል ስትራቲንክ ድረ ገፅ ፅሁፉን አጠቃሏል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy