NEWS

ኢትዮጵያ ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ፀኃፊነት እንድትመረጥ ግብጽ ትደግፋለች

By Admin

May 14, 2017

ቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ  አድሃኖም   ከምርጫ    ቅስቀሳው ጋር  በተያያዘ  ለሁለት  ቀናት የስራ   ጉብኝት   ካይሮ   ገብተዋል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ  ካይሮ  አለም አቀፍ  አየር  ማረፊያ   ሲደርሱ  የሀገሪቱ  የውጭ  ጉዳይ   የአፍሪካ  ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር  ሞሃመድ   ኢድሪስ    አቀባበል   አድርገውላቸዋል፡፡

ከውጭ  ጉዳይ  ሚኒስትሩ  ሳሜህ  ሹክሪ   በሞሃምድ   ኢደሪስ   በኩል ለቴወድሮስ  አድሃኖም  ሰላምታ  ማድረሳቸው ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ  አፍሪካን  ወክላ  ለአለም ጤና  ድርጅት  ዋና  ጸኃፊነት   ለምታደርገው  የምርጫ  ፉክክር  ሀገራቸው  ግብጽ  ድጋፍ  እንደምታደርግም ለቴድሮስ  አድሃኖም  መልዕክታቸውን  አስተላልፈዋል፡

የውጭ  ጉዳይ  ሚኒስትሩ  ከምርጫው  ጋር  በተያያዘ  ወደ  ጀኔቫ  ለሚያቀናው  የግብጽ  ልዑክ ለኢትዮጵያ  ድምጽ   እንዲሰጥም  አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ   አፍሪካን   ወክላ  ለአለም  ጤና  ድርጅት ዋና  ፀኃፊነት  ከተመረጠች   የአህጉሪቱን  ጥቅም  እንደምታስከብር  ተናግረዋል፡፡

የመጨረሻው  ምርጫ  በጀኔቫ  ግንቦት  15 እንደሚደረግም ታውቋል፡፡

ምንጭ፡- http://www.egyptindependent.com