Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በመንግስታቱ ድርጅት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ላበረከተችው አስተዋጽኦ ምስጋና ተቸራት

0 389

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የመንግስታቱ ድርጅት የሠላም ማስከበር ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሃፊ አተል ከሃር ኢትዮጵያ በሠላም ማስከበር ተልዕኮ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ምስጋና አቀረቡ።

ምክትል ዋና ፀሃፊው ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱን የተከታተሉት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም፥ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይሎች በዓለም ሠላምና መረጋጋት እንዲኖር ለከፈሉት መስዋዕትነት ምስጋና ማቅረብ የውይይቱ አጀንዳ እንደነበር ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነቷ እያደረገችው ያለው አስተዋጽኦም ሌላው የውይይቱ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዲኤታዋ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነም ኢትዮጵያ በዓለም ሠላምና መረጋጋት እንዲኖር ከመንግስታቱ ድርጅት ጋር ለመስራት ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ገልጸዋል።

በሶማሊያ ሠላምና መረጋጋት ለማምጣት በሚደረገው ጥረትም ኢትዮጵያ ከሃገሪቷ መከላከያ ኃይል፣ ፖሊስና የፀጥታ መዋቅር ጋር ተባብራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸውንም አቶ መለስ አስረድተዋል።

ምክትል ዋና ፀሃፊው በበኩላቸው ኢትዮጵያ በመንግስታቱ ድርጅት ሠላም ማስከበር ተልዕኮ የተጫወተችው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በሌሎች ሃገራት ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ኢትዮጵያውያን ሠላም አስከባሪ ኃይሎች ለከፈሉት መስዋዕትነትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በመንግስታቱ ድርጅት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን በማሰማራት ቀዳሚ ከሆኑት ሃገራት መካከል ትጠቀሳለች።

በአሁኑ ወቅት በመንግስታቱ ድርጅት ስር በሚገኙ የተለያዩ የሠላም አስከባሪ ዕዞች ከስምንት ሺህ በላይ ሠላም አስከባሪ ወታደሮች ማሰማራቷን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy