Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኮሚሽነር ዘይድ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምርመራ መርካታቸውን ገለጹ

0 324

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሀገሪቱ አንዳንድ አካባዎች ተከስተው በነበሩ ሁከቶች ዙሪያ ባካሄደው ምርመራ መርካታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የሠብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዛድ ራድ አል ሁሴን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት የሠብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዘይድ ራድ አል ሁሴን የማጠቃለያ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሀገሪቷ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ስለተፈፀመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ባካሄደው ምርመራ ደስተኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ ያደረገችው የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ ግብር ብዙ ችግሮችን እንደሚያስወግድ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል ኮሚሽነሩ።

የሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ተከስተው በነበሩ አለመረጋጋቶች በፀጥታ ኃይሎች ስለተወሰደው እርምጃና ስለ ጠፋው የሰው ህይወት ይፋ ማድረጉም ጥሩ ነው ብለዋል።

የተመድ የሠብዓዊ መብት ኮሚሽን ሁኔታውን ለመመርመር ፍቃድ ባያገኝም የአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያደረጋቸው ምርመራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ነው የጠቀሱት።

ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር “በአዲስ አበባ የሚገኘውን ፅህፈት ቤታችንን ማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመናል፤ ይህም ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ድጋፍ መስጠት ያስችለናል” ብለዋል።

ኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ፣ የዜጎቿን የመማርና ጤንነት የማግኘት መብቶች ማረጋገጥ እንደቻለች አንስተዋል።

ባልተረጋጋ ቀጣና ውስጥ ያለችው አዲሲቷ ኢትዮጵያ ከረጅም ጊዜ የአምባገነን ሥርዓት ወጥታ ያካሄደችው ሰፊ የመሰረተ ልማት ማስፋፋትና የፀረ ድህነት ትግል የሚደነቅ መሆኑንም ኮሚሽነር ዘይድ ራድ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ ሀገሪቱ በዴሞክራሲና የሲቪክ ተቋማትን በማጠናከር ረገድ የሰራችው ሥራ ከሌሎች ዘርፎች ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የዴሞክራሲና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በዘርፉ እንዲሰራም መክረዋል።

ኮሚሽነሩ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን ለማጠናከር የሲቪክ ማህበራትና የበጎ አድራጎት እንዲሁም የፀረ ሽብር አዋጆችና የሚዲያ ህጎችን መልሳ ብታያቸው የሚል አስተያየትም ሰንዝረዋል።
በአሁኑ ወቅት ከተቃዋሚዎችና ከሲቪክ ማህበራት ጋር የተጀመረውን ችግሮችን ለመፍታት ተቀራርቦ የመሥራት መርህ አጠናክሮ በመቀጠል ዴሞክራሲን ለማጎልበት እንዲሰራም ነው የመከሩት።
ምንጭ፡-ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy