NEWS

የሲንጋፖር ም/ ጠቅላይ ሚንስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

By Admin

May 06, 2017

የሲንጋፖር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ቲዎ ቺ ሀን በቀጣይ ሳምንት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ የሲንጋፖር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ጉብኝቱ የአገራቱን የሁለትዮች ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ቲዎ ቺ ሀን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላይሚንስትር  ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስለጣናት ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስት ካደረጉ የሲንጋፖር ኩባንያዎችም ጋር እንደሚገናኙ የሲንጋፖሩ ስትሬት ታይም ዘገባ ያስረዳል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ቲዎ ቺ ሀን ከኢትዮጵያ በመቀጠል ደቡብ አፍሪካን እንደሚጎበኙ ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል፡፡

ምንጭ፤ ስትሬይት ታይምስ