NEWS

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የ5.6 ሚሊዮን ዶላር ሊሰጥ ነው

By Admin

May 25, 2017

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለሶስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የውሃ እና ንጽህና አቅርቦት የሚውል የ5.6 ሚሊዮን ዶላር ብድር እና ስጦታ ሊያቀርብ ነው፡፡

ንኩ ድጋፉን ማድርግ የፈለገው የኢትዮጵያ መንግስት ለህዘቦች የተሻሻለ ኑሮ የሚሰራቸውን ተግባራት ለመደገፍ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ድጋፉ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በንፅህና እና በቆሻሻ አወጋግድ 3 ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡

ድጋፉ በ9 ክልሎች የሚገኙ ውሃ አጠር የገጠር አካባቢዎችና አርብቶ አደሮር የተመለከተ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የውሃ አቅርቦቱ በተበከለ ውሃ የሚመጡ በሽታዎችን ለመቀነስ ፋይዳ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡ ለውሃ ፍለጋ ብዙ ኪሎሜትሮችን የሚጓዙ የህብረተሰብ ክፍሎችም ድካማቸውን ለመቀነስ ድጋፉ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-የአፍሪካ ልማት ባንክ