NEWS

የክቡር የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የደስታ መግለጫ

By Admin

May 23, 2017

ክቡር ፕሪዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው በመመረጣቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገለጹ፡፡ ክቡር ፕሪዝዳንቱ ለኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡ አያይዘውም፣ ምርጫው የአገራችን ህዝቦች በጋራ በመሆን ላስመዘገቡት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጥ ጉልህ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡