Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የፍትህ መዛባት፣ መዘግየትና የዳኛን ውሳኔ በሀሰተኛ ሰነድ ማስቀየር ችግሮች ሊፈተሹ ይገባል

0 846

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የፍትህ መዛባት፣ መዘግየትና የዳኛን ውሳኔ በሀሰተኛ ሰነድ ማስቀየር ችግሮች ሊፈተሹና በትኩረት ሊታዩ እንደሚገባ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ።

ከክፍለ ከተማው 10 ወረዳዎች የተውጣጡት ነዋሪዎች ይህን ያሉት የፍትህ ሣምንትን አስመልክቶ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ነው።

በፍትህ ሥርዓቱ የሚስተዋሉ የፍርድ ውሳኔ መዘግየትና መዛነፍ፣ የዳኛ ውሳኔን በሀሰተኛ ሰነድ ማስቀየር እንዲሁም የዳኞችና ጠበቆች የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ችግሮች ላይ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

የፀጥታ ችግር፣ የትራፊክ አደጋ መባባስ፣ ፆታዊ ትንኮሳ፣ ጫትና ሲጋራን የመሳሰሉ ሱስ አስያዥ እፆች መስፋፋት የፍትህ አካላቱን ትኩረት የሚሹ አሳሳቢ ችግሮች መሆናቸውን አንስተዋል ነዋሪዎቹ።

በውይይቱ ላይ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የጉለሌ ምድብ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበራ አሰፋ የጽህፈት ቤቱን የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

የፍትህ ጽህፈት ቤቱ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የታዩ ክፍተቶች የተለዩ በመሆኑ በቀጣይ እንደሚከናወኑ አመልክተዋል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በሚፈለገው ልክ አለመፍታት እንዲሁም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራትን ከክፍተቶቹ መካከል ጠቅሰዋል።

በውይይቱ ከህዝቡ የተነሱ ችግሮችና የቀረቡ ቅሬታዎችም እንደ እጥረት የታዩ መሆናቸውን አቶ አበራ ጠቅሰዋል።

ችግሮችን ለመፍታትና ክፍተቶችን ለመሙላት የሠራዊት አቅም ግንባታና ለለውጥ ስራዎች አፈጻጸም የቅርብ ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ተግባራት ትኩረት እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።

በየደረጃው የተለዩ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሰራም አክለዋል።

የትራፊክ አደጋን መቀነስ፣ የሰው ኃይል ፍልሰትን መቀነስና ብቃት ያላቸውን ለመሳብ ጥናት መስራት፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተናበው እንዲሰሩ ማስቻልና የዕቅድ አፈጻጸምን በቅርበት መከታተልና መገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

ከህዝብ ለሚነሱ የፍትህ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ መስጠትም እንዲሁ።

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ውለታው ደሴ በበኩላቸው በመድረኩ ከህብረተሰቡ የተነሱ ችግሮች እየተጠኑ በየደረጃው ምላሽና መፍትሄ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።

የዘንድሮው 7ኛው የፍትህ ሣምንት “የሕግ የበላይነት ለዘላቂ ሠላምና ለሕዝቦች አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚከበረው።

የፍትህ ሳምንቱ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር እንዲሁም በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሚያዝያ 30-ግንቦት 6 ቀን 2009 ዓ.ም በፌደራልና በሁሉም ክልሎች ይከበራል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy