Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ድርድሩን ስኬታ ለማድረግ ኅብረተሰቡ አዎንታዊ ጫና ማሳደር አለበት – አቶ ሽፈራው ሽጉጤ

0 766

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢህአዴግና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያካሂዱትን ድርድር ስኬታማ ለማድረግ ኅብረተሰቡ አዎንታዊ ጫና ማሳደር እንዳለበት የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አመለከቱ።

ኢህአዴግ ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት በተመለከተ ፓርቲው ሕገ-መንግስቱን በህገመንግስታዊ መንገድ ለማክበር ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ በኋላ ኢህአዴግ በአገሪቷ በሕጋዊ መንገድ ከተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት፣ ክርክርና ድርድር ለማድረግ ወስኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

በዚህም በአሁኑ ወቅት ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ 17 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግና ደንቡን ተከትለው በቅድመ ሁኔታዎቹ ላይ እየተወያዩ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ሽፈራው ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት፤ ኅብረተሰቡ በገዥውም ሆነ በተቃዋሚዎች ላይ አዎንታዊ ጫና መፍጠር አለበት።

ሁሉንም ነገር በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ፣ በነጻ ሀሳብ በመግለጽ እንዲፈጸም የህዝቡ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

እንደ አቶ ሽፈራው ገለጻ፤ በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተጀመረው ድርድር ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በድርድሩም ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግና መሰረትን ባከበረ መልኩ በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ አቀራረብ በውይይቱ ላይ የነቃ ፖለቲካዊ ተሳታፊ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ይሁንና በውይይቱ ማንኛውም ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ የሃሳብ ልዩነታቸውን ጠብቀው እርስ በእርስ የመደማመጥና የመከባበር እሴቶችን በማዳበር የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢህአዴግንም ጨምሮ በድርድሩ የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት አቋማቸውን ሳይለቁ መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም ነው አቶ ሽፈራው ያመለከቱት።

ይህንን ማድረግ የሚቻል ከሆነ መቀራረብ አልያም ደግሞ ልዩነቱን ለሚወክሉት ሕዝብ በማቅረብ ኅብረተሰቡም በሂደቱ አዎንታዊ ጫና  እንዲጫወት እድል መስጠት አለበት ነው ያሉት።

ኅብረተሰቡም በፖለቲካ ደርድሩ ወስጥ የሚያነሳቸውን ማንኛውም ዓይነት ጥያቄዎችና አስተያየቶች “ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በማቅረብ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው” ብለዋል።

ከሠላም ውጪ ምንም አማራጭ እንደሌለ የተናገሩት አቶ ሽፈራው፤ “ከጥፋት ምንም የሚተርፍ ነገር የለም፤ በጥፋትና ሁከት የለማ አገር፣ ህዝብ የለም” በማለትም ኅብረተሰቡን አሳስበዋል።

የሃሳብ ልዩነት በሰላማዊ መልኩ እንዲስተናገድና መደማመጥ እንዲኖር ሕዝቡን መሰረት አድርገው የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመሪነት ሚናውን መጫወት እንዳለባቸው ሃሳብ ሰጥተዋል።

በዚህም የተረጋጋ ስኬታማ የመድበለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የተረጋጋ ምጣኔ ሃብት እንዲሁም ሰላምና ደኅንነቱ የተጠበቀ አገር መገንባት እንችላለን በማለት እምነታቸውን ጠቁመዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን በአገሪቷ የመድብለ ፖለቲካ ፓርቲን ለማስፋት የሚያደናቅፉ የአመለከካትና የአሰራር ሥርዓቶችን ለመመከት መንግሥት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለዚህም ደግሞ በፌዴራልና በክልል የሲቪክ ማኅበራት መድረኮችን በመክፈት የተለያዩ ሃሳቦችን ለማስተናገድ የሚችል ብሔራዊ የፖለቲካ ምህዳር ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ “አሁን ላይ ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል ተዘጋጅተናል ወይንም አልተዘጋጀንም ማለት አይደለም፤ አጀንዳ አላቀረብንም” ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል አጀንዳ እንዳልቀረበና አሁኑ ላይ ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል በሚለው ጉዳይ ላይ ሃሳብ መስጠት አግባብ እንዳልሆነም አቶ ሽፈራው ገልጸዋል።

በጥልቅ ተሃድሶ የተለዩ ጉዳዮችን መልስ በመስጠት የተሻለ የሕዝብ እርካታን ለማረጋገጥ ፓርቲያቸውና መንግሥት በጋራ በመሆን በቅድሚያ እየሰራ መሆኑንም ነው ያስረዱት።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy