ጂቡቲ በ590 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያስገነባችው ዘመናዊ የዱራህሌ ወደብ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በ960 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዶራሌ ሁለገብ ወደብ ለተለያዩ አገልግሎቶች ይውላል ተብሏል።
ወደቡ 590 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የፈጀ ሲሆን ወጪው በጂቡቲ ወደብ እና በቻይና መርቻንትስ ሆልዲንግስ በተባለ ተቋም ተሸፍኗል᎓᎓
የኢትዮያን 95 ከመቶ የሚሆነው የወጪ እና የገቢ ንግድ የሚተላለፈው በጂቡቲ ነው᎓᎓ ከዚህ በተጨማሪም ለብዙ የውጭ አገሮችና ለተለያዩ ተቋማት ወታደራዊ ይዞታ ሁና እያገለገለች ነው᎓᎓
ጂቡቲ አዲሱ በምትገነባው ዶራሌ ሁለገብ ወደብ ወደብ አልባዋ ደቡበ ሱዳን ከጦርነት ወጥታ ሰላም በሆነችበት ጊዜ እንደምትጠቀምበትም ተስፋ አድርጋለች᎓᎓
ወደቡ በዓመት እስከ ሰላሳ ሽህ የሚሆኑ መርከቦችን ያስተናግዳል ተብሏል።
ምንጭ:-ዥንዋ