CURRENT

ገንዘቤ ዲባባ በኢዩጅን የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸነፈች

By Admin

May 27, 2017

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በአሜሪካ ኢዩጅን የአምስት ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸነፈች።

ገንዘቤ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 14 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ከ22 ማይክሮ ሰከንድ ወስዶባታል።

ገንዘቤ ትናንት ምሽት ውድድሩ ከመካሄዱ በፊት በእህቷ ጥሩነሽ ዲባባ የተያዘውን የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በመስበር ጭምር እንደሚታሸንፍ ተናግራ ነበር።

ይሁንና ገንዘቤ ውድድሩን ስታሸንፍ የገባችበው ሠዓት ክብረ ወሰኑን እሰብረዋለሁ ካለችውና ጥሩነሽ ዲባባ ካስመዘገበችው 14 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ከ15 ማይክሮ ሰከንድ የዓለም ክብረ ወሰን በ14 ሰከንድ የዘገየ ነው።

በትናንቱ የኡጂን የሴቶች የአምስት ሺህ ሜትር ሩጫ ገንዘቤን ተከትላ የገባችው ኬንያዊቷ ሊሊያን ካሳይት ስትሆን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 14 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ ከ80 ማይክሮ ሰከንድ ወስዶባታል።

ውድድሩን ሶስተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና የኔዘርላንድስ ዜግነት ያላት ሲፋን ሀሰን ነች።

ገለቴ ቡርቃና ደራ ዲዳ አራተኛና አምስተኛ ሆነው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።