የኢቲቪው ጋዜጠኛ ስራውን ለቀቀ ወይስ ተባረረ?
ትላንት አርብ ጠዋት የኢቲቪ ማኔጅመንትን ባካተተው ስብሰባ ያለ ሀላፊዎች እውቅናና ይሁንታ ቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ መደረጉን ኮንኖ በዚህ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ ማስተላለፉን ምንጮች ገልፀው ጋዜጠኛውን ጨምሮ በመዝናኛ ክፍሉ ሀላፊና ማስታወቂያውን በድርጅቱ ድረ ገፅ ላይ ባወጣው ሰራተኛ ላይ ቅጣት እንዲፈፀም ተወስኗል። ይህ ውሳኔ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ግን ገዜጠኛ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባቱ ተሰምቷል። ተሰብሳቢዎቹ ከስብሰባ ውስጥ ሳይወጡ ጋዜጠኛው የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባቱ በድርጅቱ ሀላፊዎች ዘንድ ድንጋጤ ፈጥሯል ተብሏል።