Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር ተወያዩ

0 302

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቀጣናው የማምረቻ ኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን በሚያግዛት የሰው ሃብት ልማት ዙሪያ ከጃፓን ጋር እንደምትሰራ ተናግረዋል።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ መሆኑን የገለጹት አቶ ደመቀ፥ በሰው ሃብት ልማት በጋራ መስራታቸው ግንኙነታቸውን ወደ ተሻለ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው አክለዋል።

ጃፓን በምርምር እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ የደረሰችበት የእድገት ደረጃ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሊጣጣም በሚችል መንገድ ልምድ ያገኘችባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

abie_and_demeke.jpg

በአቤ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት ለአፍሪካ ሀገራት የሰው ሃይል አቅም ግንባታ በምታደርገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ተጠቃሚነት እንዲጎለብትም ጠይቀዋል።

በአፍሪካ አህጉር የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ያላት ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታደርገውን ሁለንተናዊ ጥረት እንደሚያደንቁ ተናግረዋል።

በቀጠናውና ከቀጠናው ውጪ ባሉ የዓለም ክፍሎች በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ የምታደርገው ጥረት ሊበረታታ ይገባልም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገችው ያለውን የካይዘን ፍልስፍና ውጤታማነት በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማስፋፋት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

በቀጣይም የጃፓን ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ በስፋት እንዲገቡና የኢትዮጵያ ምሁራንና ተመራማሪዎችም በጃፓን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ በቅንጅት ለመስራትም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ በጃፓን ባደረገው የስራ ጉብኝት የተለያዩ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ምርምር ተቋማትን መጉብኘቱን ኢዜአ በዘገባው ጠቅሷል fbc

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy