Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሠላም በህዝብ ባለቤትነት እውን የሚሆን ነው!

0 226

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሠላም በህዝብ ባለቤትነት እውን የሚሆን ነው!

                                                             ደስታ ኃይሉ

እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ የሰላምን ጥቅም የሚገነዘብ ያለ አይመስለኝም። ይህ ህዝብ ለሰላም የከፈለው ዋጋ እጅግ ከፍተኛ ነው። መንግስት ሰላምን በተመለከተ አንድ አዋጅ ሲያወጣ ፈጥኖ የአዋጁ ባለቤት የሚሆነው ለዚሁ ነው። ከዚህ አኳያ ህዝቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ከማስፈፀም ባለፈ በየአካባቢው የሰላሙ ባለቤት ሆኖ እየተንወሳቀሰ መሆኑን ማየት እንችላለን።

እንደሚታወቀው ሁሉ በአዋጅ ጊዜያዊ መፍትሔ ካልሆነ ዘላቂ ሰላምን እውን ማድረግ አይቻልም። ለአገራችን ሰላም መረጋገጥ መሰረቱ ህዝቡ ነው። ይህ በመሆኑም ምክንያት የአገራችን ሰላም በአጭር ጊዜ ወደነበረበት የተመለሰው ህብረተሰቡ ለሰላም ካለው ፅኑ ፍላጎት እንጂ በአዋጁ ብቻ አይደለም። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ወቅት የየአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ያሳየው ኃላፊነት ሊጠቀስ የሚገባው ነው። ይህም የሰላሙ ባለቤት ህዝቡ ራሱ መሆኑን የሚያስረዳ ነው።  

እንደሚታወቀው ሁሉ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች በውጭ ሃይሎችና በሀገራችን የውስጥ ተላላኪዎቻቸው ቅንጅታዊ እኩይ ሴራ ሁከት ተፈጥሮ ነበር። ሁከቱን በቁጥጥር ስር ማዋል እንዲቻልም በህገ መንግስቱ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወጥቷል። ይህ አዋጅም በወቅቱ ሰላሙን ተነጥቆ በነበረው የየአካባቢዎቹ ህዝቦች በባለቤትነት ስሜት ድጋፍ ያለው ስለነበረ ከፍተኛ ውጤት ማግኘት ተችሏል።

በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከህዝቡ ጋር በመሆን የተፈጠረውን ሁከት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። የሁከቱ ተሳታፊ የነበሩ ወገኖችም የተሃድሶ ትምህርት ወስደው በሁለት ዙሮች ተመርቀዋል። በሁከቱ ወቅት የበደሉትን ህዝብ ለመካስ ቃል በመግባትም ወደየመጡበት አካባቢዎች ተመልሰዋል።

በቅድሚያ እነዚህን አጥፊ ዜጎች በመጠቆምና ለእርምት ወደ ተሃድሶ ማዕከሎች እንዲገቡ በማድረግ ረገድ የህዝቡ የማይተካ ሚና እዚህ ላይ ሊደነቅ የሚገባው ይመስለኛል። ይህም ማንኛውም አዋጅ ያለ ህዝቡ የባለቤትነት መንፈስ ተፈፃሚ ሊሆን እንደማይችል የሚያረጋግጥ ነው።

ለአዋጁ ስኬታማነት ግንባር ቀደም ተዋናዩ ህዝቡ ነው። ህዝቡ በማንኛውም መስፈርት ሰላሙን ተፃርሮ ሊቆም አይችልም። በመሆኑም ለሰላሙ እውን መሆን አጥፊዎችን በማጋለጥና በመገምገም የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል። አጥፊዎች ተሃድሶ ትምህርት ወስደው ሲመለሱም ዕውቀት ገብይተው መመለሳቸውን ስለሚገነዘብም ድጋፍና ክትትል አድርጓል። ይህም ህዝቡ ለሰላሙ ምን ያህል ቀናዒ መሆኑን የሚያሳይ ተግባር ይመስለኛል።

የትኛውም ሀገር ሰላም በህዝብ ፍላጎት እንጂ በአዋጅ አይጠበቅም። ስለ ሰላም በሚደረጉ ማናቸውም ክንዋኔዎች ውስጥ የህዝቡ ተሳትፎ ፋና ወጊ ነው። የሀገራችንንና የህዝቦቿን ሰላምና መረጋጋት የማይሹ የውጭ ሃይሎችና የውስጥ ተላላኪዎቻቸው የፈፀሙት ፀረ-ሰላም ድርጊት የት ድረስ እንደ ዘለቀ ከህዝቡ የተሰወረ እውነታ አይደለም። ህዝብ ሁሌም ከማንኛውም ተግባር በፊት ግራና ቀኝ የሚያይ፣ ህጋዊ አካሄዶችን በማጤንና አሉታዊና አዎንታዊ ጎኑን በመገንዘብ ሚዛናዊ ውሳኔ የመስጠት ባሀል ያለው ነው።

ህዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታው የሚወሰነው ሀገራችን በምትከተለው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ መሆኑን ስለሚያውቅ ሁሌም ሰላም ወዳድ ኃይሎች ጋር የሚቆም ነው። የሰላምን ጠቀሜታ ስለሚገነዘብም ከምንግዜውም በላይ ሁሌም በየአካባቢው ለሰላሙ  ዘብ እንደቆመ ነው።

ህዝቡ በየቀየው ላለው የሰላም ሁኔታ ዋነኛ መሰረት ነው። በዚያ አካባቢ ለሚከሰት ማናቸው የፀረ-ሰላም ድርጊት መልሶ የሚጎዳው እርሱን በመሆኑ ለሰላሙ ይበልጥ መትጋት አለበት። እንዲህ ዓይነቱ ሰላምን የሚያጎሉ፣ ልማትን የሚያፋጥኑና ንትርክን የሚያስቀሩ መንገዶችን መከተል ባይቻል ኖሮ፤ የመጀመሪያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን እውን ማድረግና ህዝቡም የተጀመረውን የፀረ-ድህነት ዘመቻ አጠናክሮ ባልቀጠለ ነበር።

ከልማት ዕቅዱም በየደረጃው ተጠቃሚ ሆኖ ተፈላጊውን የዕድገት ራዕይ ሰንቆ ባልተጓዘም ነበር። አሁን እያለመ ላለውና ከመጀመሪያው ዕቅድ ጋር ተመጋጋቢ የሆነውን ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድንም ባላለመ ነበር።

በዚህ ደረጃ ላይ ሆኖ የተጀመረውን ዕድገት ለማስቀጠልና በዚያውም ልክ ዴሞክራሲው ሀገር በቀል ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲጎለብት የተደረገው ጥረት፤ እንዳለ ሆኖ ይህ ህዝብ በአንዳንድ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች ውስጥ ከመልካም አስተዳድር ጋር እንዲሁም ፅንፈኛ ኃይሎችና የሀገራችንን መለወጥ የማይሹ አንዳንድ ወገኖች አማካኝነት የተከሰተውን ሁከት ለመቋቋም ህዝቡ በባለቤትነት ስሜት የከፈለው መስዕዋትነት በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ይህ የህዝቡ ስሜት የመነጨው ከምንም ተነስቶ አይደለም— የሰላምን እሴት በምንም ሊለካው እንደማይችል ያለፉት ተጨባጭ ሂደቶች ስላስተማሩት እንጂ።

አዎ! ከተግባር የበለጠ ትምህርት ቤት ባለመኖሩም፤ ይህ ህዝብ የሰላሙ ዘብ ሆኖ ቆሟል። ሁከቱን ለመቀልበስ በሀገራችን የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የህዝቡን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥና ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ሲባል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአስፈጻሚው አካል ታውጆ ተግባራዊ ሲሆንም ይህ ህዝብ የአንበሳውን ድርሻ ተጫውቷል። በዚህ የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ በሀገራችን ላይ ተደቅኖ የነበረው አደጋ እንዲቀለበስ ለማድረግ በተደረገው ርብርብ የህዝቡ ሚና ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።

ይህ ሰላም ወዳድ ህዝብ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሰላምን በማወክ ተግባር ላይ የተገኙ ወጣቶችን በመገሰፅ፣ ለሰላም እንዲሰሩና የሰላምን እሴት እንዲያውቁ እንዲሁም በቅርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ባደረገው ግምገማ ሂደቱን ደረጃ በደረጃ ወደ መደበኛው የህግ ማስከበር የአሠራር ስርዓት የሚያሸጋግር ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ እንዲወጣ በማድረግ ረገድ ህዝቡ ያከናወናቸው የገዘፉ ተግባራት የህዝቡ መገለጫዎች ናቸው።

ይህ ህዝብ ላለፉት 26 ዓመታት ገደማ የተራመዳቸው የልማት አባጣና ጎርባጣ ውጣ ውረዶች በአሁኑ ወቅት የሚቀራቸው ተጨባጭ ለውጦች ቢኖሩም፤ ከትናንቱ በተሻለ ቁመና እንደሚገኙ ያውቃል። እርሱንም በተሻለ ማማ ላይ እንደሚያወጡት በልማቱ ውስጥ ተዋናይ የሆነው ማንኛውም ዜጋ በየደረጃው ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱን ራሱን ዋቢ አድርጎ መቅረብ የሚችል ህዝብ ነው።

ትክክለኛ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ካሉ፣ ህዝቡን ከዳር እስከ ዳር የሚያንቀሳቅስ ልማታዊ መንግስት ካለና በዚሁ መሪ አካል አስተባባሪነት ብሎም በህዝቡ የባለቤትነት መንፈስ የሚዘወር ሰላም እስካለ ድረስ፤ ሰርቶ መለወጥና ማደግ እንደሚቻል ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው። ለዚህም ነው በየአካባቢው የሰላሙ ዋስና ጠበቃ ሆኖ እየሰራ የሚገኘው። ይህ አኩሪ ተግባሩም ወደፊት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy