Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በትግራይ በስራቸው የተሻለ አስተዋጽኦ ላደረጉ 755 የፖሊስ አመራሮችና አባላት የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ

0 689

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በትግራይ ክልል በስራቸው የተሻለ አስተዋጽኦ ላደረጉ 755 የማረሚያ ቤቶች ፖሊስ አመራሮችና አባላት ዛሬ ከሪቫን እስከ ወርቅ ሜዳሊያ የሚደርስ የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

ሽልማቱን ያበረከቱት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አባይ ወልዱ እንዳሉት፣ዜጎችን ወደ ስህተት እንዳይገቡ አስቀድመው በማስተማርና የተሳሳቱንም በማረም የተጀመረው ያልተቆጠበ ትግል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

“ሌሎች አባላትም የተሸላሚዎቹ መልካም አርአያና ጀግንነት ሊከተሉ ይገባል “ብለዋል።

የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ተወካይ ኮማንደር ወልዳይ አብራሃ በበኩላቸው የፖሊስ አመራሮችና አባላቱ ለሽልማት የበቁት ከሰባት እስከ 25 ዓመት ባገለገሉበት ወቅት በዕለተ ተዕለት ስራቸውና በመልካም ስነ ምግባራቸው የተሻለ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ነው፡፡

ከተሸለሙት መካከል 161 ያህሉ ሴት አመራሮች ናቸው

ኮማንደር ህይወት ነጋሽ የመቀሌ ማረሚያ ቤት የታራሚዎች አስተባባሪና ከተሸላሚዎቹም መካከል አንዱ ሲሆኑ የደርግ ስርዓትን ለመደምሰስና ለህዝብ እኩልነት ሲሉ ከህወሓት ጎን ተሰልፎው በጽናት መታገላቸውን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡

አሁንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እያገለገሉ መሆናቸውንና ሽልማቱም ለበለጠ ስራ እንደሚያተጋቸው ተናግረዋል፡፡

ከዓዲግራት ማረሚያ ቤት ተሸላሚ የሆኑት ኮማንደር ኪዳነ ሀፍተ በበኩላቸው በተበረከተላቸው ሽልማት ሳልኩራሩ ለበለጠ ውጤት ጠንክረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

በግለኝነትና በሙስና ለሚታዩ ችግሮች በጽናት በመታገል አርአያ ለመሆን እንደሚጥሩም አመልክተዋል፡፡

በሽልማት አሰጣጡ ስነስርዓት ላይ ከፌዴራል፣ ከክልልና ከዞን የተወከሉ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy