Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አስራ አምስት ብር ከኪስ ውስጥ አውጥቶ ሲወስድ እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ ።

0 2,653

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አስራ አምስት ብር ከኪስ ውስጥ አውጥቶ ሲወስድ እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ ።

ተከሳሽ ስንታየሁ ነጋሽ ሽሽፋ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፊ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 665/1/ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ተከሳሽ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ ግንቦት 29/2009 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02/03 ክልል መርካቶ ሰላም ባልትና እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ የግል ተበዳይ አዳነች አሳ ለብሰው ከነበረው የቱታ ሹራብ የግራ ኪስ ውስጥ የነበረ የኢትዮጵያ አስራ አምስት ብር አውጥቶ ሲወስድ እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው የስርቆት ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል ።

የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ወንጀል ችሎት ተከሳሹ ክሱን እንዲከላከል ሲጠይቀው ተከሳሹ “በወቅቱ የግል ተበዳይ ከኪሷ ብር ሲወድቅባት አንስቸ ልሰጣት ስል ሌባ ሌባ ብለው ያዙኝ እንጂ አኔ አልሰረቁም በተመሰረተብኝ ክስም ጥፋተኛ አይደለሁም ”ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ለፍርድ ቤቱ ሰጧል ።


ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሳሽን ጥፋተኛነት ያረጋግጥልኛል ያላቸውን የሰው መስክሮችና ተሰረቀ የተባለው አስራ አምስት ብር በኢግዚቪትነት ፖሊስ ጣቢያ ተይዞ ስለሚገኝ ፍርድ ቤቱ ሰኔ 09/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ ነህ ብሎታል።
የቅጣ ውሳኔው ደረጃ 1 እርከን 6 ላይ ያርፋል ማክበጃ አልቀረበም ማቅለያ ተከሳሹ ከዚህ በፊት ሪከርድ የለለበትና የቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆኑ በእርከን አምስት ስር ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊወችን ያስተምራል በሚል በአንድ ዓመት ፅኑ እራትና በአንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር እንዲቀጣ ወስኖበታል ።

ዘገባውየፌደራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነዉ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy