ከኢትዮጵያ የማምረቻ ዘርፍ ፖሊሲ በርካታ ስኬታማ ተሞክሮዎችን እንዳገኙ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ ለውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከሆኑት የአፍሪካ ሀገራት በተሻለ ደረጃ ላይ እንደምትገኝም ተነግሯል፡፡
ሀገሪቱን ተመራጭ ካደረጓት ምክንያቶች መካከል አነስተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት መኖር፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታና የመሰረተ ልማት መስፋፋት ዋንኛው ነው ተብሏል፡፡
ዘርፉን በይበልጥ ለማሳደግ ከተፈገ ደግሞ የሚያስፈልገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራት እንዳለባት ነው የተነገረው፡፡
በአፍሪካ የማምረቻ ዘርፍን በማሳደግ ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡