Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በጅቡቲና ኤርትራ ድንበር የተከሰተውን ውጥረት አገሮቹ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱት ጥሪ አቀረበች

0 559

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ  በጅቡቲና ኤርትራ ድንበር መካከል የቆየው የኳታር ሰላም አስከባሪ ኃይል ከቦታው በመልቀቁ ምክንያት የተከሰተውን ውጥረት አገሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው የፕሬስ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያ ኳታር የሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ከጅቡቲና ኤርትራ ድንበር ካስለቀቀች በኋላ በአገሮቹ መካከል የተከሰተውን ውጥረት በቅርበት እየተከታተለች ነው።

ኢትዮጵያ ትናንት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት፤ በአገራቱ መካከል የተከሰተውን ውዝግብ ለመፍታት ጉዳዩን የሚያጣራ እውነታን ፈላጊ ልዑክ እንዲሰማራ ያቀረቡትን ሀሳብ እንደምትደግፍ መግለጫው አስታውቋል።

አገራቱ የተነሳውን ውዝግብ ከማባባስ ተቆጥበው ያላቸውን ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እንደምትፈልግ የጠቆመው የቃል አቀባዩ መግለጫ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውጥረቱን ለማርገብ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደምታበረታታ አትቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy