Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በ2017 ከአፍሪካ አገራት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች:- የአለም ባንከ

0 661

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ  በተያዘው የአውሮፓውያኑ በ2017 ከአፍሪካ አገራት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እንደምታስመዘግብ የአለም ባንክ ገለጸ።

“ግሎባል ኢኮኖሚክ ፕሮስፔክት” በዚህ ወር ባቀረበው ሪፖርት እንዳመለከተው ኢትዮጵያ በተያዘው የአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ዓ.ም 8.3 ከመቶ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች።

ታንዛኒያ 7.2 ከመቶ አይቬሪኮስት 6.8 ከመቶ ሴኔጋል ደግሞ 6.7 ከመቶ እድገት በማስመዝገብ ኢትዮጵያን ይከተላሉ ብሏል።

የአለም ባንክ እንደገለፀው በተፈጥሮ ሃብት ያልተመሰረተ ኢኮኖሚ ያላቸው አገራት ኢኮኖሚው ጥንካሬውን ይዞ የመቆየት እድል አለው᎓᎓ በመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት፣ በጠንካራ የአገልግሎት ዘርፍ እና በእርሻ ምርት መስፋፋት ስለሚታገዝ ነው ይላል ሪፖርቱ᎓᎓

የአገሪቱ የህዝብ ብዛትም ሌላው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማደግ የሚረዳ  ነው ተብሏል።

አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ባለፈው ሚያዝያ ወር ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በተከታታይ ባስመዘገበችው አመታዊ ጥቅል ምርት ኬንያን በመብለጥ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የኢኮኖሚ ባለቤት መሆኗ ማመልከቱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ  አመታዊ ጥቅል ምርት  በአውሮፓውያኑ 2016 ከነበረው 72 ቢሊዮን ዶላር   በ2017  ወደ 78  ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድግ  አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ትንበያ አመልክቷል።

ምንጭ:-አፍሪካ ኒውስ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy