Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ የኢ-ቪዛ አገልግሎት ጀመረች

0 618

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በኢንተርኔት መመዝገብ የሚችሉበት አሰራር ተግባራዊ ተደረገ።

አሰራሩ ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ሳይጉላሉ፥ በቀጥታ ኢንተርኔት በመመዝገብ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች መምሪያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድም አሰራሩን በጥምረት ማዘጋጀታቸውን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በዚህ መሰረት መንገደኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባት ሲፈልጉ፥ ባሉበት ቦታ ሆነው በተፈቀደ የማመልከቻ ድረ ገጽ በመግባት ከተመዘገቡ በኋላ ለማመልከቻቸው በኢሜል አድራሻቸው ምላሽ ይሰጣል።

ባገኙት ምላሽ መሰረትም የበረራ አገለግሎቱን የሚያገኙ ይሆናል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አሰራሩ የሃገሪቱን ቱሪዝም፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ያበረታታል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ለመንገደኞች ጊዜ እና ወጪን በመቆጠብ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ያገኙ ዘንድ ያስችላቸዋልም ነው ያሉት።

አየር መንገዱ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ በረራዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመስጠት፥ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ ማድረጉን እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ገብረዮሃንስ ተክሉ በበኩላቸው፥ በአገልግሎቱ መጀመር የተሰማቸወን ደስታ ገልጸዋል።

ሃላፊው አያይዘውም ተቋማቸው የመንገደኞችን የጉዞ ሂደት ማቀላጠፍ የሚያስችል አሰራር እንደሚከተልም ገልጸዋል።

ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች አገልግሎቱን ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ማግኘት የሚችሉ ይሆናል።FBC

https://www.evisa.gov.et/#/home

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy