ባለፉት 5 ዓመታት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር (አልማ) አስታወቀ።
ማህበሩ 12ኛ መደበኛ ጉባኤውንና 25ኛ ዓመት የብር ኢዩቤልዩ በዓሉን በባህር ዳር እያከበረ ነው።
የማህበሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ብስራት ጋሻው ጠና እንደገለጹት፥ ማህበሩ በከልሉ እየተከናወኑ ላሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች አጋር ሆኖ እየሰራ ነው።
ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥም የአባላቱን ቁጠር ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ወደ 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ማድረስ ችሏል ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ።
ከአባላትና ከአጋር አካላትም ባለፉት 5 ዓመታት ወስጥ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉም ተገልጿል።
በቀጣይም ማህበሩ በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች ሁሉም ባለደርሻ አካላት ድጋፋቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል ወይዘሮ ብስራት ጋሻው ጠና።
በሙሉጌታ ደሴ