Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2010 ዓመታዊ ረቂቅ በጀት ከ320 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ

0 896

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2010 ዓመታዊ ረቂቅ በጀት ከ320 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ።ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው በ2010 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀትን 320 ቢሊዮን 803 ሚሊዮን 602 ሺህ 160 ብር ሆኖ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ከሃምሌ 1 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በሚፈጸመው በአንድ የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች 81 ቢሊዮን 839 ሚሊዮን 528 ሺህ 570 ብር እንዲሁም 114 ቢሊዮን 703 ሚሊዮን 641 ሺህ 453 ብር ደግሞ ለካፒታል ወጪዎች ይውላል።

117 ቢሊዮን 260 ሚሊዮን 432 ሺህ 137 ብር ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ሲሆን፥ 7 ቢሊዮን ብሩ ደግሞ ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ እንዲውል ተመድቧል።በጀቱ እንዲጸድቅም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቷል።

ምክር ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈበት የ2010 በጀት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ9 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ አለው።ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው በጤናው ዘርፍ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ለሚከናወን ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ከአለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተፈረመው የብድር ስምምነት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ አዋጆቹ እንዲጸድቁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላልፏል።

 

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy