Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የትግራይ ሰማዕታት ቀን በመቐለ ሰማዕታት ሃውልት ተዘክሯል

0 1,572

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በ17 አመታት የተካሄደው የትግል መስዋዕትነት በኢትዮጵያ ብዝሃነት ተከብሮ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲተከል ማድረጉን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባሳደር አዲስአለም ባሌማ ተናገሩ።

የትግራይ ሰማዕታት ቀን ዛሬ በመቐለ ከተማ በሰማዕታት ሃውልት ተዘክሯል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የትጥቅ ትግሉ በሃገሪቱ ብዝሃነት ተከብሮ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲተከል አድርጓል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ የተሻለ ለውጥ እንድታስመዘግብ አድርጓታልም ነው ያሉት።

የተጀመረውን ልማት መደገፍም የሰማዕታቱ ካሳ ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል።

በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ በረከት ስምኦን በበኩላቸው፥ የትግራይ ህዝብ ትግል መላው ኢትዮጵያውያንን ያነሳሳ እንደነበር ገልጸዋል።

የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴንም አሁን ላይ የሚስተዋሉትን የትምክህት፣ ጠባብነትና አክራሪነት አስተሳሰቦችን፥ ከትግራይ ህዝብና ከህወሃት ጎን በመሆን እንደሚዋጋም ነው የገለጹት።

በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙትና ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎችም ከደደቢት በረሃ ጀምሮ ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የሃገር ሽማግሌዎቹ እንዳሉት፥ የትጥቅ ትግሉ ታሪክ ወጣቱ ትውልድ እንዲማርበት ሊሰራ ይገባል።

በዛሬው የሰማዕታት ቀን ዝክር ላይ በክልሉ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ 831 ጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች ሽልማት ተበርክቷል።

ከዚህ ውስጥ 263ቱ ወደ መካከኛ ባለሃብትነት መሸጋገራቸውም በሽልማት ስነ ስርዓቱ ወቅት ተጠቅሷል።

በሰማዕታቱ ዝክር ላይ የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሰማዕታት ቤተሰቦች፣ የአጋር ድርጅት አመራሮችና መስራቾች እንዲሁም ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

ታዳሚዎቹ በመቐለ ከተማ ሰማዕታት ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

የትግራይ ሰማዕታት ቀን በ1980 ዓ.ም ሰኔ 15 ቀን የደርግ የጦር አውሮፕላኖች፥ በሃውዜን ለገበያ በወጡ ንጹሃን ዜጎች ላይ ያደረሱትን ጭፍጨፋ እና የ17 አመቱን የትጥቅ ትግል ለመዘከር በየአመቱ ሰኔ 15 ቀን ይከበራል።

በሙሉጌታ አጽብሃ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy