ለኢትዮጵያ በተደራጀ መንገድ ድጋፍ እንደሚያበረክቱ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለፁ᎓᎓
ከሃያ የተለያዩ ግዛቶች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የህዳሴው ምክር ቤት ተወካዮቸ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በተዘጋጀው የምክክር መድረክ
ላይ ተሳትፈዋል᎓᎓
የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይገድበን በኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ ላይ የራሳችንን ድርሻ ለመወጣት የህዳሴው ምክር ቤት ጥሩ ድልድል ሁኖናል ብለዋል በምክክር መድረኩ ላይ ያገኘናቸው ተሳታፊዎች᎓᎓
አላማው በዚህ ምክር ቤት አማካኝነት ልማት ወደ ሃገር ቤት የሚገባበትን መንገድ መፍጠር ነው በማለትም ገልጸዋል᎓᎓
ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የዲያስፖራ ተሳትፎ ዘርፍ ሃላፊ አቶ መርከቡ በየነ የምክክር መድረኩ በቀጣይ የበለጠ ተደጋግፈን ስንሰራ ምን ላይ ትኩረት ሰጥተን ስንሰራ የተሻለ ዲያስፖራውን ተደራሽ ማድረግ እንችላለን ብለዋል EBC