Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለእናቶችና ሕፃናት ሞት ቅነሳ የሚውል የ150 ሚሊዮን ዶላር ብድር ተገኘ

0 291

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የጤናውን ዘርፍ መደገፍ የሚያስችል የ150 ሚሊዮን ዶላር ብድር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የቀረበውን የብድር ረቂቅ አዋጅ ተመልክቶ ለዝርዝር እይታ ለበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

የብድር ፕሮግራሙ ቀድሞ የተጀመረውን ውጤትን መሰረት ያደረገ የፋይናንስ ስርዓት ፕሮግራም በማስቀጠል የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ ይውላል።

የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መለስ ጥላሁን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መግለጫ ብድሩ የተገኘው ከዓለም አቀፍ ልማት ማህበር መሆኑን ተናግረዋል።

የብድሩ ዓላማም በጤና ዘርፍ የተያዘውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የልማት ግቦች በተለይም የእናቶችና ህፃናትን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማሻሻል የሚውል መሆኑን ገልፀዋል።

የጤና ሽፋን ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች በማዳረስ በጤናው ዘርፍ የተያዙትን እቅዶች ለማሳካት እንደሚያግዝም ነው ያስረዱት።

በተጨማሪም የወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲን በማጠናከር የነዋሪዎችን ምዝገባ በአግባቡ ለማከናወን ይረዳልም ብለዋል።

ከዓለም አቀፍ ልማት ማህበር ከተገኘው 150 ሚሊዮን ዶላር ብድር በተጨማሪ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም 20 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ከፓወር ኦፍ ኑትሪሽን ትረስት ፈንድ 20 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተገኝቷል።

በብድር የተገኘው 150 ሚሊዮን ዶላር ስድስት ዓመት የእፎይታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመት የሚመለስ መሆኑም ተገልጿል።

ረቂቁ አዋጅ ቁጥር 15/2009 የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ለተጨማሪ ምልከታ ለበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy