NEWS

ማይክሮሶፍት በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሶፍት ዌር ማበልፀጊያ አካዳሚ ሊከፍት ነው

By Admin

June 02, 2017

ማይክሮሶፍትና አለምአቀፉ የጤና ፍትሃዊነት ማዕከል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሶፍት ዌር ማበልፀጊያ አካዳሚ በወሎ ዩኒቨርሲቱ ሊከፍቱ ነው፡፡

የተለያዩ መተግበሪያዎች ወይም አፕልኬሽንና ክህሎት ማምረቻ የሚሆነው አካዳሚው  በኢትዮጵያ ያለውን የዘርፉን  አቅም ለማሳደግ ያግዛል ተብሏል፡፡

ማይክሮሶፍት አፍሪካና አጋሩ አለምአቀፉ የጤና ፍትሃዊነት ማዕከል  የከፈቱት አካዳሚ  በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ተያያዥ የሳይንስ ዘርፎች የሚመረቁ የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን  ለስድስት ወራት ያህል ተቀብሎ ያሰለጥናል ፣ወደ ስራ አለም ከመቀላቀላቸው በፊት  አስፈላጊ ክህሎቶችን የሚቀስሙበት ማዕከል ሆኖ ያጋለግላል ተብሏል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎቹ በቆይታቸው ከማይክሮሶፍት የዳበረ ልምድ ካላቸው  የሶፍት ዌር መሃንድሶች ጋር በመስራት የልምድ ሽግግርም ያገኛሉ ተብሏል፡፡

በአለምአቀፉ የጤና ፍትሃዊነት ማዕከልና በማይክሮሶፍት አፍሪካ የሚከፈተው አካዳሚ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲሆን ከአፍሪካ ደግሞ 9ኛው ነው፡፡

አካዳሚው በተቋቋመባቸው ደቡብ አፍሪካ ፣ ግብፅ፣ ናይጀሪያ ፣ ሩዋንዳና ጋና እስካሁን 300 የሶፍት ዌር ጠበብቶችን አስመርቆ ወደስራ አስገብቷል፡፡

አካዳሚው በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ግቢ ተቋቁሞ ስራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኮምቦልቻ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሳይንስ ዳይሬክተር አቶ አህመዲን ሙሀመድ  ከማይክሮ ሶፍት ጋር ችግር ፍቺ የቴክኖሎጂ ስራዎችን በመስራት ማህበረሰባዊ ህይወትን በሚያቃልሉ ዘርፎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ ቬንቸር በርን