Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሽብር ድርጅት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመሳተፍ ወንጀል ከተከሰሱ 16 ግለሰቦች ውስጥ 13ቱ ጥፋተኛ ተባሉ

0 328

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በሽብር ድርጅት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመሳተፍ ወንጀል ከተከሰሱ 16 ግለሰቦች ውስጥ 13ቱ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈ።

ተከሳሾች 1ኛ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን፣ 2ኛ በላይነህ ሲሳይ፣ 3ኛ አለባቸው ማሞ፣ 4ኛ አወቀ ሞኜ፣ 5ኛ ዘሪሁን በሬ፣ 6ኛ ወርቅዬ ምስጋናው፣ 7ኛ አማረ መስፍን፣ 8ኛ ተስፋዬ ታሪኩ፣ 9ኛ ቢሆነኝ አለነ፣ 10ኛ ተፈራ ፈንታሁን፣ 11ኛ ፈረጄ ሙሉ፣ 12ኛ አትርሳው አስቻለው፣ 13ኛ እንግዳው ዋኘው፣ 14ኛ አንጋው ተገኘ፣ 15ኛ አግባው ሰጠኝ እና 16ኛ አባይ ዘውዱ ናቸው።

የጠቅላይ አቃቢ ህግ ክስ እንደሚያመለክተው ተከሳሾች ከ2004 ዓ.ም በፊት የመኢአድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የነበሩ ናቸው።

ከ2004 እስከ የካቲት 2006 ዓ.ም ደግሞ ራሱን አርበኞች ግንቦት ሰባት ብሎ የሚጠራው የሽብር ቡድን አባል መሆናቸው በክሱ ተጠቅሷለ።

ተከሳሾች በአማራ ክልል ባህርዳርና ጎንደርን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች በመንቀሳቀስ የሃገሪቱን መረጃ ለሽብር ቡድኑ በማቀበል አባላትን በመመልመል ወደ ኤርትራ መላካቸውም በክሱ ተዘርዝሯል።

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት በመቅረብም የቀረበባቸውን ክስ ክደው ተከራክረዋል።

ከሳሽ አቃቢ ህግም ተከሳሾቹ ከሽብር ቡድኑ ጋር ሲለዋወጡ የነበረውን የሰነድ ማስረጃና የሰው ምስክር ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ አሰምቷል።

ሆኖም አቃቢ ህግ በ5ኛ፣ 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች ላይ ያቀረበው የሰነድ ማስረጃና የሰው ምስክር ተከሳሾቹን ወንጀለኛ የሚያስብል አይደለም ሲል ፍርድ ቤቱ በነጻ አሰናብቷቸዋል።

በዛሬው እለትም በቀሪ ተከሳሾች ላይ የቀረበባቸው የሰነድ ማስረጃና የሰው ምስክር ተገቢ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ አሳልፏል።

የቅጣት ውሳኔ ለመስጠትም ለሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy