Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአምቦ ከተማ መሃን የተባለችው በቅሎ ወልዳለች

0 4,267

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ በቅሎ ወልዳለች።

ንብረትነቷ የከተማዋ ነዋሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ድንቁ የሆነችው በቅሎ፥ እየተጠናቀቀ ባለው የግንቦት ወር ነው የወለደችው።

በተደጋጋሚ የማይከሰተው የበቅሎዋ የመውለድ ዜና የአካባቢውን ነዋሪዎችም አስገርሟል።

አሳዳሪዋ የሆኑት አቶ ተስፋዬ በቅሎዋን ከጊንጭ በመግዛት ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ መተዳደሪያቸው ለሆነውና ለሚሰጡት የጭነት አገልግሎት ሲጠቀሙባት ነበር።

ጋሪ እየጎተተች የጭነት አገልግሎቱን የምትሰጠው በቅሎ አካላዊ ሁኔታ እየተቀየረ ይመጣል።

አሳዳሪዋም የበቅሎዋን ሆድ ካለወትሮው ማደግና በየጊዜው መጨመር በመመልከት ምናልባት አርግዛ ይሆናል በሚል ወደ እንስሳት ሃኪም ለመውሰድ ማሰባቸውን ለጎረቤቶቻቸው ያማክራሉ።

ጎረቤቶቻቸው በአንጻሩ በቅሎዋ እንዴት ታረግዛለች በሚል የአሳዳሪዋን ግምት ያጣጥሉታል።

አሳዳሪዋም በቅሎዋን በአካባቢው ወደሚገኝ የእንስሳት ህክምና መስጫ በመውሰድ ካሳዩ በኋላ፥ ማርገዟ ይነገራቸዋል።

ሁኔታው ያልተለመደ ቢሆንም በቅሎዋ ጊዜዋን ጠብቃ ወልዳለች።

የአምቦ ወረዳ የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት የእንስሳት ህክምና ዶክተር ምስጋና ለሜ፥ በሳይንሱ በቅሎ የክሮሞዞም እጥረት ስላለባት መውለድ እንደማትችል ይናገራሉ።

ይሁን እንጅ አልፎ አልፎ ያለ ክሮሞዞም እጥረት ሙሉ ሆነው የሚፈጠሩ በቅሎዎች ስለሚኖሩ መውለድ እንደሚችሉም ተናግረዋል።

ዶክተር ምስጋና እንደሚሉት ይህ አጋጣሚ ግን አነስተኛና ምናልባት በረጅም ጊዜያት አንድ ጊዜ የሚፈጠር ነው።

እንደ ኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘገባ፥ በክልሉ ከዚህ በፊት በምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳ ቀኝ ወረዳ በቅሎ ወልዳ ነበር።

በያዝነው ወር መጀመሪያ ደግሞ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ በቅሎ መውለዷን መዘገባችን ይታወሳል። FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy