Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በጎንደር ከተማ ሽብር በመፈፀም የሰው ህይወት ያጠፉና ንብረት ያወደሙ ተጠርጣሪዎች ክስ ተመሰረተባቸው

0 353

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በጎንደር ከተማ እና አካባቢው ሽብር በመፈፀም የሰው ህይወት ያጠፉና ንብረት ያወደሙ 10 ተጠርጣሪዎች ክስ ተመሰረተባቸው።

1ኛ ተከሳሽ ክንዱ ዱቤ፣ 2ኛ ዘመኑ ጌቴ፣ 3ኛ ደበበ ሞገስ ጨምሮ 10 ግለሰቦች ናቸው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ የመስረተባቸው።

ተከሳሾቹ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የአድማ ስምምነት በማድረግ ራሱን የአርበኞች ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራው የሃገር ውስጥና የውጭ አባላት ጋር ግንኙነት በማድረግ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን እና በአዲስ አበባ መንቀሳቀሳቸውን ክሱ ያስረዳል።

ከ1ኛ እሰከ 3ኛ ያሉት ተከሳሾች በጎንደር ከተማ በመገናኘት የፋይናንስ ክፍል ሃላፊና አሰተባባሪ፣ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊና የፖለቲካና ፕሮፖጋንዳ ሃላፊ በሚል የስራ ክፍፍል ማድረጋቸውንም ነው ጠቅላይ አቃቤ ህግ በክሱ ያመለከተው።

በታህሳስ 2007 ዓ.ም እና በህዳር 2009 ዓ.ም በውጭ ከሚገኘው የሽብር ቡድን አባላት 400 ሺህ ብር በመቀበል የሽብር ተግባር ለመፈፀም የጦር መሳሪያ፣ ጥይቶች፣ ቦምብና ሌሎች ቁሳቁሶች መግዛታቸው ተጠቅሷል።

350 ክላሽ፣ ጥይቶች እና አራት ኤፍ ዋን ቦምቦች ከተገዙት የጦር መሳሪያዎች ውስጥ ይገኙበታል።

በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓል እንዳይከበር የተለያዩ የአመፅ ቅስቀሳ ወረቀቶች በማዘጋጀት እንዲበተን ማድረጋቸው በክሱ ተጠቅሷል።

ጥር 1 ቀን እና 2 2009 በጎንደር ከተማ ጃንተከል መናፈሻና ኢንታሶል ሆቴል ቦምቦችን በመወርወር የአንድ ስው ህይወት እንዲያልፍ፣ በ19 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት እንዲደርስ እና ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸውንም ክሱ ያሳያል።

በተለይም በአማራ ክልል የተፈጠራው ሁከትና ብጥበጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት፣ ደባርቅ፣ ታች አርማጭሆና በተለያዩ የአካባቢው ወረዳዎች የአመፅ ወረቀት በመበተን ንብረት እንዲወድም አድርገዋል ይላል ክሱ።

ወደ ጠገዴ፣ ፀገዴ እና ዑመራ የሚሄድ ማንኛውም ተሽከርካሪ እያስቆሙ እንዲያቃጥሉ እና ድርጊቱን ለሚፈፅሙ ሰዎችም የገንዘብና የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተወያይተው ተልዕኮ ሰጥተዋል የሚለው የአቃቤ ህግ ክስ፥ ለሽብር ቡድኑ ሰባት አባላትን በመመልመል ወደ ኤርትራ ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ መላካቸውንም ጠቁሟል።

በአጠቃላይ አስሩም ተከሳሾች የሽብር ቡድን አባል በመሆን በሽብር ደርጊት መሳተፍ ወንጀል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ አቅርቦባቸዋል።

አቃቤ ህግ በፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው የወንጀል ችሎት ነው ክስ ያቀረበው።

ተከሳሾቹ ከጠበቃቸው ጋር እንቀርባለን በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ክሱን በዝርዝር ጠበቃዎቻቸው በተገኙበት በንባብ ለማሰማት ለሰኔ 14 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።FBC

በበላይ ተስፋዬ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy