Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ትናንት እና ዛሬ ከ1 ሺህ 400 በላይ ዜጎች ከሳዑዲ አዲስ አበባ ገብተዋል

0 285

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ ከ1 ሺህ 400 በላይ ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሳዑዲ አረቢያ ህጋዊ የስራ እና የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሀገሪቱ የሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የ90 ቀናት የምህረት አዋጅ ማወጇ ይታወሳል።

የምህረት አዋጁን ተከትሎም አዋጁ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ሀገሪቱን ለቀው ለመውጣት እንቅሰቃሴ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ቀደም ብሎ ከ20 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን መንግስት መግለጹ ይታወሳል።

ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስም 1 ሺህ 465 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ተነስተው አዲስ አበባ መግባታቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ተገኝቶ ተመልክቷል።

የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ፥ ከሳዑዲ ተመላሾች አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ወደ ክልል ሲጓዙ እና አዲስ አበባ ሲቆዩ እንግልት እንዳይደርስባቸው በመንግስት ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ተመላሾቹ እንደ ሌሎች ዜጎች ሁሉ በራሳቸው ስራ ፈጠራ፣ በንግድ፣ በግብርና ወይም በሌሎች ዘርፎች ላይ ሰርተው መኖር እንዲችሉ በፈቃዳቸው ላይ የተመሰረተ አደረጃጀትና ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ተናግረዋል።

ከሳዑዲ አረቢያ እንዲወጡ የታዘዙ ኢትዮጵያውያንን የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃላፊ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በየዕለቱ ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች የጉዞ ሰነድ በመውሰድ ላይ የሚገኙ ሲሆን፥ እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች የጉዞ ሰነድ እንደወሰዱ ነው የተነገረው።

በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ የዜጎች አስመላሽ ግብረ ሃይል ወደ ሳዑዲ በመሄድ ከሀገሪቱ ንጉስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ዜጎች እንዲወጡ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መነጋገራቸው ይታወሳል።

መጋቢት 21 2009 ዓ.ም የተጀመረው የምህረት አዋጅ ሰኔ 20 2009 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy