Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ቻይና በአፍሪካ መሰረተ ልማትና ትምህርት ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ልታደርግ ነው

0 335

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ቻይና በአፍሪካ በመሰረተ ልማትና በትምህርት ዘርፎች  በርካታ ቢሊዮን ዶላር በማፍሰስ ለአህጉሪቱ ያላትን አጋርነት እያሳየች መሆኑ ተነግሯል፡፡

ቻይና ቀጣይ ኢኮኖሚ እድገቷን ለማረጋገጥ ከአፍሪካ የተለያዮ ጥሬ እቃዎችን ወደ ሀገሯ ስታስገባ በብዙ ቢሊዮን ዶላር በሚቆጠር ወጪ በአህጉሪቱ መሰረተ ልማትና ትምህርት መስኮች ላይ ታፈሳለች ነው የሚባለው፡፡

ለአብነትም ቻይና በአፍሪካ በባቡር፣ መንገድ፣ ወደብ፣ በቴሌኮሚኒኬሽን እና በሌሎችም ዘርፎች 60 ቢሊዮን ዶላር ታፈሳለች ተብሏል፡፡

በትምህርት መስክም በአሁን ወቅት ቻይና ለ60 ሺህ አፍሪካዊያን ነፃ የትምህርት እድል እየሰጠች ሲሆን ይህ አህዝ በቀጣይ ሶስት ዓመታት ውስጥ ወደ 100 ሺህ ለማድረስ እየሰራች እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

ባለፉት 20 ዓመታት ቻይና ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድ አጋርነት በ40 እጥፍ እንዳሳደገች ነው የሚነገረው፡፡

እ.ኤ.አ በ2009 አፍሪካ የቻይና ቀዳሚ የንግድ አጋር ስትሆን የሀገሪቱ ሁለተኛዋ የድፍድፍ ነዳጅ ምንጭ እደሆነች ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ፦ ኤቢሲ ኔት ድረ-ገጽ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy