የቻይና ከፍተኛ የህግ አውጭ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ እና ከአርጀንቲና ጋር ወንጀለኞችን ለመቀያየር የተደረጉትን ስምምነቶች አፀደቀ፡፡
የቻይና ብሔራዊ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ እስረኞችን በሚቀያየሩ አገራት ሀላፊነት፣ ግዴታዎች፣ አስፈላጊ ወጪዎች እንዲሁም ግጭቶችን መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ነው ውሳኔውን ያሳለፈው፡፡
የአቻይናው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሊዩ ዜንሚን ስምምነቶቹ ከቻይና ህግ ጋር የማይቃረኑና የቻይናን ጥቅም የሚያስከብሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያና ቻይና ስምምነቱን ከሶስት አመታት በፊት እኤአ 2014 ግንቦ ወር ውስጥ ነበር የተፈራረሙት፡፡
ምንጭ፡- ሽንዋ