Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅቶችና ጋዜጠኞች ኢትዮጵያን እየጎበኙ ናቸው

0 1,479

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅቶችና ጋዜጠኞች የኢትዮጵያን ቱሪዝም መዳረሻዎችን እየጎበኙ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት አለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅቶችና ጋዜጠኞችን የሀገሪቱን ዋና ዋና መስህቦች በማስጎብኘት ላይ ነው፡፡

ለኢትዮጵያ ቱሪዝም አመንጪ ከሆኑ አገራት የተመረጡ 18 ሰዎች ጉብኝቱን እያከሄዱ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከነዚህም መካካል የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ኢንዱኒዥያ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይና ናይጄርያ ድርጅቶቹና ጋዜጠኞቹ የተውጣጡባቸው አገራት ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ ያደረገችው የቱሪዝም መዳረሻዎች በተሟላ መልኩ ይገልፃል ተብሎ አዲስ ይፋ የተደረገውን የቱሪዝም መለያ ማስተዋወቅ የጉብኝቱ ዋና አላማ መሆኑ ታውቋል፡፡

እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዝየም፣ ቅድስተ ስላሴ ካቴድራል፣ ጎንደር ፋሲለደስ እንዲሁም ጣና ሃይቅና በሃይቁ ላይ የሚገኙት ጥንታዊ ገዳማት ተጎብኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የሆኑ የዕምቅ የቱሪስት መስህቦች መገኛ መሆኗን ጎብኝዎቹ ገልጸዋል፡፡

ጉብኝቱ ቀጥሎ ዛሬ አክሱም የተደረሰ ሲሆን በቀጣይም በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቱሪስት ይጎበኛሉ፡፡

የኢትዮጵያና የአለም አቀፉ አስጎብኚ ድርጅቶች የሚያደርጉት የንግድ ለንግድ ስምምነት የጉብኝቱ ማጠቃለያ እንደሚሆን ሪፓርረታችን ስብሃት ግርማ ከስፍራው ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy