NEWS

አሰግድ ተድፋዬ ከዚህ አለም በሞት ተለየ- ፈደሬሽኑ

By Admin

June 04, 2017

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የነበረው አሰግድ ተስፋዬ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢቢሲ በላከው መግለጫ  አስታወቀ፡፡

አሰግድ ተስፋዬ በመልካም ስነ-ምግባሩና በልዩ ችሎታው የአገራችንን እግር ኳስ አፍቃሪዎች የማረከ፣ ሀገራችንን በክብር ያስጠራና ለወጣት ተጫዋቾች ምሳሌ በመሆን በግንባር ቀደምነት ከሚጠቀሱት  የእግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደ ነበር አብራርቷል፡፡

ህፃናትን በማሰልጠን ለሀገራችን እግር ኳስ ትንሳኤ ሳይታክት በመስራት ላይ እያለ በሞት በሞት በመለየቱ ምክንያት ፈዴሬሽኑ የተሰማውን ሃዘን ገልጿል፡፡

እንዲሁም ለመላው የአገራችን እግር ኳስ ስፖርት ቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ ፌዴሬሽኑ መፅናናትን ተመኝቷል፡፡