NEWS

አስራ አምስት ብር ከኪስ ውስጥ አውጥቶ ሲወስድ እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ ።

By Admin

June 30, 2017

አስራ አምስት ብር ከኪስ ውስጥ አውጥቶ ሲወስድ እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ ።

ተከሳሽ ስንታየሁ ነጋሽ ሽሽፋ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፊ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 665/1/ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ተከሳሽ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ ግንቦት 29/2009 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02/03 ክልል መርካቶ ሰላም ባልትና እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ የግል ተበዳይ አዳነች አሳ ለብሰው ከነበረው የቱታ ሹራብ የግራ ኪስ ውስጥ የነበረ የኢትዮጵያ አስራ አምስት ብር አውጥቶ ሲወስድ እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው የስርቆት ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል ።

የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ወንጀል ችሎት ተከሳሹ ክሱን እንዲከላከል ሲጠይቀው ተከሳሹ “በወቅቱ የግል ተበዳይ ከኪሷ ብር ሲወድቅባት አንስቸ ልሰጣት ስል ሌባ ሌባ ብለው ያዙኝ እንጂ አኔ አልሰረቁም በተመሰረተብኝ ክስም ጥፋተኛ አይደለሁም ”ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ለፍርድ ቤቱ ሰጧል ።

ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሳሽን ጥፋተኛነት ያረጋግጥልኛል ያላቸውን የሰው መስክሮችና ተሰረቀ የተባለው አስራ አምስት ብር በኢግዚቪትነት ፖሊስ ጣቢያ ተይዞ ስለሚገኝ ፍርድ ቤቱ ሰኔ 09/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ ነህ ብሎታል። የቅጣ ውሳኔው ደረጃ 1 እርከን 6 ላይ ያርፋል ማክበጃ አልቀረበም ማቅለያ ተከሳሹ ከዚህ በፊት ሪከርድ የለለበትና የቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆኑ በእርከን አምስት ስር ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊወችን ያስተምራል በሚል በአንድ ዓመት ፅኑ እራትና በአንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር እንዲቀጣ ወስኖበታል ።