Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና ግብጽ በሱዳኑ ፕሬዚዳንት ላይ የተጀመረው ምርመራ እንዲቋረጥ የጸጥታው ምክር ቤትን ጠየቁ

0 261

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ እና የግብጽ ዲፕሎማቶች የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ላይ በዘር ማጥፋት ወንጀል ዙሪያ ያቀረበውን ክስ እንዲያቋርጥ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤትን ጠየቁ፡፡

ለመንግስታቱ ድርጅት የጽጥታው ምክር ቤት ትላንት ዳርፉርን አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት፥ የአለም አቀፉ ፍርድ አቃቤ ህግ ፋቱ ቤንሱዳ 15 አባል ሀገራት ያሉትን የጸጥታው ምክር ቤትን በዳርፉር ዘር ጭፍ ጨፋ ፣የጦር ወንጀሎች እና በሰው ልጆች ለተፈጸሙወንጀሎች ተጠርጣሪ ናቸው የሚላቸውን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ አምባሳደር ተቀዳ አለሙ በቀረበው ሪፖርት ላይ በሰጡት አስተያየት ፥ፍርድ ቤቱ በአፍሪካውያን ላይ የሚከተለውን አሰራር አፍሪካ ሀገራትን እያስከፋ ያለ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የአለም አቀፉን ፍርድ ቤት በሱዳኑ ፕሬዚዳንት ላይ የጀመረውን ምርመራ እንዲያቋርጥ የአፍሪካ ህብረት መጠየቁን ያስታወሱት አምባሳደር ተቀዳ ፥የፍርድ ቤቱ ድርጊት ግጭቱን ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ አፍሪካዊ መፍትሄዎችን የማፈላለግ ጥረትን የሚያዳፍን ነው ብለዋል፡፡

የዳርፉርን ግጭት እንዲያበቃ ብርቱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን እና የሰላም ሂደቱ መሻሻሎች እያሳያ ቢመጣም ብዙ እንደሚቀር አምባሳደር ተቀዳ ተናግረዋል፡፡

የጸጥታው ምክር ቤት ተፋላሚ ወገኖች ላይ ጫና በማሳደር የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ያሳሰቡት አምባሳደር ተቀዳ ፥ የዳርፉር አማጺያን ቡድኖች ደግሞ የጦር መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደ ሰላም እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመንግስታቱ ድርጅት የግብጽ አምባሳደር እና ቋሚ ተወካይ አሚር አብዱላጢፍ አብዱላታ በበኩላቸው በፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ላይ ፍርድ ቤቱ የጀመረውን ክስ እንዲያቋርጥ ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የአፍሪካን ሰላም እና ጸጥታ አደጋ ላይ እንዳይጥል ሊጠነቀቅ ይገባል ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ዳርፉርን በተመለከተ የጸጥታው ምክር ቤት ከጉዳዩ እጁን እንዲያወጣ ጥሪ ቢያቀርብም ፥እስካሁን ከጸጥታ ምክር ቤቱ ምላሽ አለመገኘቱ ተዘግቧል፡፡

ምንጭ ፦ ሱዳን ትሪቡን

በእስክንድር ከበደ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy