Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የአቶሚክ ሃይልን ለሰላማዊ አላማዎች መጠቀም የሚያስችላትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመች

0 800

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የአቶሚክ ሃይልን ለሰላማዊ አላማዎች መጠቀም የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

በዘጠነኛው አለም አቀፍ አቶሚክ አውደ ርዕይ ላይ የተፈረመው ስምምነት፥ ሃገራቱን የአቶሚክ ሃይልን ለሰላማዊ አላማዎች መጠቀም በሚያስችላቸው የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሰሩ የሚያስችል ነው።

ስምምነቱን የኢፌዴሪ የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አፈወርቅ ካሱ፥ ከሩሲያው ሮሳቶም አቶሚክ ኢነርጅ ኮርፖሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኒኮላይ ስፓስኪ ጋር ተፈራርመዋል።

በሁለቱ ሃገራት መካከል የተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት የአቶሚክ ሃይልን ለሰላማዊ አላማዎች ለማዋል የተፈረመ የመጀመሪያው ስምምነት ነው።

ስምምነቱ በኒውክሌር መሰረተ ልማት ግንባታና በኒውክሌር ቴክኖሎጂና አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት፥ በኢንዱስትሪ፣ ህክምናና ግብርና ዘርፎች የሬዲዮ አክቲቭና የጨረራ መተግበሪያ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ ያስችላል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በኒውክሌር፣ በራዲዮሎጅ ህክምና፣ በመሰረታዊና በተግባር የታገዙ ምርምሮች፣ በሰው ሃይል ስልጠና እና በኒውክሌር ምርምር ዘርፎች በትብብር ለመስራት እንደሚያስችልም ነው የተመለከተው።

ምንጭ፦ africabusinesscommunities.com

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy