Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ውዝግብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ ድጋፍ ታደርጋለች- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

0 526

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በኳታርና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

ኢትዮጵያ በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በአንክሮ ስትከታተል መቆየቷን ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

መንግስት በየትኛውም መንገድ እና ቅርጽ የሚፈፀምን የአሸባሪነት ተግባር እንዲሁም ለአሸባሪ ድርጅቶች የሚሰጥን ድጋፍ አጥብቆ የሚኮንን ሲሆን፥ ይህን ዓለም አቀፍ የደህንነት ስጋት ከሚታገሉ ሀገራት ጎን ሆኖ እንደሚታገል በመግለጫው አንስቷል።

ኢትዮጵያ በሀገራት ላይ አለመረጋገት የሚፈጥር ማንኛውም አይነት አፍራሽ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ አትደግፍም ነው ያለው።

ሀገሪቱ በባህረ ሰላጤው ሀገራት የተፈጠረው ችግር በሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍታት አስፈላጊ መሆኑን እንደምታምን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፥ የኩዌት ኤሚር ሼክ ሳባህ አል አህመድ አል ሳባህ የጀመሩትን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ትደግፋለች ብሏል።

ኢትዮጵያ በባህረ ሰላጤው አካባቢ ያለው ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለች አቋሟን እንደምትገልፅና ሰላም ለማምጣት ለሚደረገው ጥረት የበኩሏን ገንቢ ሚና እንደምትጫወት በመግለጫው አመላክቷል፡፡FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy