ኢትዮጵያ የዓለም የስራ የድርጅት የስራ አስፈጻሚ መደበኛ አባል ሆና ተመረጠች፡፡ በጄኔቭ በተካሄደውና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ የተመራ የልዑካን ቡድን በተገኘበት ምርጫ ኢትዮጵያ አፍሪካን ወክላ ከፍተኛ ድምጽ አግኝታለች፡፡
ኢትዮጵያም ከድርጅቱ ጋር ያላትን ግንኙነትን በማጠናከር፣ በተለይ በወጣቶች ሥራ ፈጠራ ላይ በማተኮር መንግስት 10 ቢሊዮን ብር በመመደብ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ የሚያስችል የቴክኒክ እና የፓሊሲ ድጋፍ ለማጎልበት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ ቀጣይ ራእይ ለማስቀመጥ ሰፊ ስራዎች እያከናወነ ባለበት ወቅት ሀገራችን የስራ አስፈጻሚ መደበኛ አባል ሆና መመረጧ የሀገራችንን ብሎም የአፍሪካን ጥቅም እና ፍላጎት ከግምት የሚያስጠብቅ እንዲሆን ለማድረግ ይረዳል፡፡
ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ስራ አስፈጻሚ መደበኛ አባል ሆና ለመጨረሻ ጊዜ ያገለገለችው ከእ.ኤ.አ ከ1999 እስከ 2002 ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
ሰኔ 8 ቀን 2009 ዓ.ም