Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዕቅዱ ኢንቨስትመንትንና ቁጠባን ያበረታታል!

0 512

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዕቅዱ ኢንቨስትመንትንና ቁጠባን ያበረታታል!

                                                         ደስታ ኃይሉ

ሀገራችን የቀየሰችውን የገበያ መር ምጣኔ ሃብት ሥርዓትን ተከትሎ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ተነድፎ በሥራ ላይ ውሏል፡፡ በዚህም በኢኮኖሚው ውስጥ የመንግሥት ሚና የተለያዩ የልማት ኃይሎችን በማቀናጀት መምራት፣ መሠረተ ልማት በማቅረብና የሰው ሀብት ልማትን በማካሄድ እንዲሁም ፈጣንና ውጤታማ የመንግሥት አገልግሎት በመስጠት ለልማታዊ የግሉ ዘርፍ ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠርና የመደገፍ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮችን መዝጋት እና በግሉ ሴክተር የማይሰሩ የልማት ሥራዎችን መንግስት ገቢራዊ እንዲያደርጋቸው የሚያስችሉ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል፡፡

ባለፉት ሥርዓቶች የወጡና የግሉን ዘርፍ ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚገቱ ህጎችና ደንቦች እንዲወገዱ ተደርገዋል፡፡ በዚህም ለውስጥም ሆነ ለውጭ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል፡፡ የንግድና ኢንቨስትመንት ፖሊሲን ሥር ነቀል በሆነ መልኩ በመለወጥ መንግሥት በየጊዜው የተለያዩ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ በየጊዜው ከታዩ ልምዶች ትምህርት በመውሰድ ጥንካሬዎቹን የማጎልበት ድክመቶቹን የማረም ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩም መምጣታቸው የአደባባይ ምስጢር ነው።

በህገ- መንግሥቱ የሚፈለገው ዓይነት ፈጣን ዕድገት ደግሞ ልቅ በሆነ የገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት ብቻ ሊረጋገጥ የማይችል በመሆኑ ካለፈው ትምህርት መውሰዱ ተገቢ ይሆናል። ልቅ የሆነ የገበያ ሥርዓት ዘላቂና ሰፊ መሰረት ያለው ዕድገት የማምጣት አቅም የለውም። ይልቁንም የህዝብንና የመንግሥትን አቅሞች ወደ ኪራይ ሰብሳቢነት እንዲሰማሩ የማድረግ አቅሙ የሰፋ ነው።

በመሆኑም በሂደት መንግሥት የማይተካ ልማታዊ ሚና የሚጫወትበት የነፃ ገበያ ሥርዓት መከተል እንደሚገባ ታምኖበት ገቢራዊ በመሆን ላይ ይገኛል። በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ወቅት ኢንቨስትመንትን ከማስፋፋት ጎን ለጎን በቁጠባም ረገድ አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል። የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚጠይቀው የኢንቨስትመንት መጠን ከፍተኛ ነው።

አንዱና ዋነኛው ፈታኝ ጉዳይ ለኢንቨስትመንቱ መሸፈኛ የሚያስፈልገው የአገር ውስጥ ፋይናንስ ግኝት እንደሆነ ይታወቃል። በተለይም በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ የቁጠባ መጠን መሻሻል የሚታይበት ቢሆንም ያን ያህል አጥጋቢ ባለመሆኑ፤ ልማቱን ለማስፈጸም የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በከፊል ለማቅረብ እንዲቻል የአገር ውስጥ የቁጠባ ምጣኔው በከፍተኛ ደረጃ ማደግ እንደሚኖርበት ይታመናል፡፡

ታዲያ ይህን የሀገር ውስጥ ቁጠባን የማሳደግ ግብ ለማሳካት በመጀመሪያው ዕቅድ ዘመን በርካታ የማሻሻያ ርምጃዎች መወሰዳቸውን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥም የህብረተሰቡን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ የማስተማርና የማነሳሳት እንቅስቃሴዎች፣ የፋይናንስ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸውን ተቋማት የማስፋፋት፣ የወለድ ምጣኔን የማሻሻል፣ የግል ማህበራዊ ዋስትና አገልግሎትን የመዘርጋት፣ የመንግስት የማህበራዊ ዋስትና ሽፋንን ይበልጥ እንዲጠናከር የማድረግ፣ የቤት የቁጠባ ፕሮግራም የማከናወን እና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቁጠባ ቦንድና ሌሎች በጅምር ላይ ያሉ የቁጠባ ዘዴዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

እንዲሁም የመንግስት ወጪን በዋነኝነት የካፒታል ክምችት ለሚፈጥር የኢንቨስትመንት ወጪ በመመደብ በቁጠባ ለታለመለት ዓላማ ለማዋል የተደረገው ጥረት የአገር ውስጥ ቁጠባ ከፍ እንዲል አግዟል፡፡ እነዚህ የሀገር ውስጥ ቁጠባን ለማሳደግ የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት አስገኝተዋል፡፡

ይህ መልካም የሚባል የኢንቨስትመንት አፈፃፀም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ወቅት ይበልጥ ጎልብቶ ውጤታማ መሆን ያለበት ይመስለኛል፡፡ እስካሁን በታየው የቁጠባና ኢንቨስትመንት አፈጻፀም ረገድ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ቢኖርም ቅሉ፤ አሁንም መጠኑ የማይናቅ ኢንቨስትመንት በአገር ውስጥ ቁጠባ ገንዘብ ሳይሆን በውጪ አገር ቁጠባ ገንዘብ መሸፈኑ ከጉዳዩ አኳያ ቀዳሚ ተግዳሮት ይመስለኛል፡፡ ታዲያ ይህ ተግዳሮት እየሰፋ የሚሄድ ከሆነ ለውጪ ተፅዕኖ የሚያጋልጠንና የፖሊሲ ነፃነት የሚያሳጣን ከመሆኑም ባሻገር፣ አስተማማኝና ዘላቂ የመሆን ዕድሉም የመነመነ ነው፡፡

ስለሆነም የዜጎችን እና የንግድ ድርጅቶችን ቁጠባ ከፍ ለማድረግ እስካሁን የታየውን አበረታች እንቅስቃሴ አጠናክሮ ማስቀጠል ወሳኝ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ከዚህም አኳያ የዋጋ ግሽበትን ማረጋጋትና ወደ ዝቅተኛ አሃዝ መለወጥ፣ ህዝቡን ማስተማርና ማነሳሳት፣ የቁጠባ መሳሪያዎችና አገልግሎቶችን ማስፋፋትና ማጠናከር እንዲሁም የምጣኔ ሃብት ዕድገቱን ማፋጠንና የሥራ ዕድልን ይበልጥ የማስፋፋት ጉዳዩች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

የመንግስት ቁጠባን በተመለከተም የሚገኘው የመንግሥት ገቢም ሆነ የቁጠባ ገንዘብ ውጤታማ፣ ከብክነት የፀዳ እና በግልፅ ቅደም ተከተል ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑም ትኩረት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ የመንግስት ፕሮጀክቶችን የማስፈፀም አቅም በማሳደግ የሚካሄዱትን ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች ውጤታማነትና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ዕውን ማድረግ አገራዊው የቁጠባና የኢንቨስትመንት ሁኔታን ማጠናከር ስለሆነም ከዚህ አኳያ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሚገባው ይመስለኛል።

እንደሚታወቀው ለዘላቂና ፈጣን ዕድገቱ ምቹ የሆነ የማክሮ ምጣኔ ሃብት ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ በኢንቨስትመንትና በቁጠባ መካከል ያለው ሚዛን ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ በሁለተኛው የዕቅድ ዘመን የፈጣን ዕድገቱ አንዱ ምንጭ ኢንቨስትመንት እንዲሆን ተተልሟል፡፡ በተለይም በማኑፋክቸሪንግና በግብርና፣ በመሠረተ-ልማት፣ በማህበራዊ ልማት ዘርፎችና በሌሎች መስኮች የሚከናወኑ የግልና የመንግስት ኢንቨስትመንቶች ፈጣን ዕድገትን በማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ ታቅዷል፡፡

በመሆኑም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ እስካሁን የተመዘገበውን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ምጣኔ ጠብቆ ለመሄድ በዕቅድ ተይዟል፡፡ ለዚህ ከፍተኛ ግምት ላለው ኢንቨስትመንት መሸፈኛ የሚያስፈልገው ፋይናንስ በአብዛኛው ከአገር ውስጥ ለማሰባሰብ ካልተቻለ ደግሞ የፈጣን ዕድገቱ ዘላቂነት አደጋ ላይ መውደቁ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ እናም በኢንቨስትመንትና በአገር ውስጥ ቁጠባ መካከል ያለውን ሚዛን ለማመጣጠን የአገር ውስጥ ቁጠባን በተጀመረው አቅጣጫ ማሳደግ የግድ የሚል ይመስለኛል፡፡

የአገር ውስጥ ቁጠባን ለማሳደግ በተጠናቀቀው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በርካታ ርምጃዎች ተወስደው ውጤት ማስገኘት ጀምረዋል፡፡ በተያዘው የዕቅድ ዘመንም የተወሰዱትን ርምጃዎች አሟልቶ በመተግበር ከጠቅላላ ኢንቨስትመንቱ ቢያንስ ሁለት-ሦስተኛውን በአገር ውስጥ ቁጠባ መሸፈን ይቻል ዘንድ በዕቅድ ዘመኑ የአገር ውስጥ ቁጠባ ምጣኔውን ወደ 29 ነጥብ 6 በመቶ ለማድረስ ተተልሟል፡፡

የመንግስትን ቁጠባ ለማሳደግ የመንግስት በጀት በዋነኝነት የካፒታል ክምችት ለሚፈጠር የኢንቨስትመንት ወጪ የመመደብ እና የመንግስት በጀትን በቁጠባና በውጤታማነት ጥቅም ላይ የማዋል ፖሊሲዎች በያዝነው የዕቅድ ዘመን ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ይመስለኛል፡፡ ቀደም ሲል ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የመንግስትም ሆነ የግል ቁጠባ ውጤታማ፣ ከኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር በፀዳ እና በግልፅ ቅደም ተከተል ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን መጨረሻ ኢንቨስትመንት ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የሚኖረው ድርሻ 41 ነጥብ 3 በመቶ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ከጠቅላላው የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ በ2007 ከነበረበት 80 ነጥብ 5 በመቶ በ2012 ወደ 70 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተንብዩዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ የዕቅድ ዘመን የወጪ ንግድ ገቢ አገልግሎትን ጨምሮ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ከፍተኛ ዕመርታ በማሳየት በ2007 ከነበረበት 12 ነጥብ 8 በመቶ በ2012 ወደ 20 ነጥብ 6 በመቶ ያድጋል። የገቢ ንግድ ወጪ አገልግሎትን ጨምሮ በ2007 ከነበረት 29 ነጥብ 6 በመቶ በ2012 ወደ 32 ነጥብ 3 በመቶ ከፍ ይላል፡፡ በዚህ መሠረትም የሃብት ክፍተት ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ በ2007 ከነበረበት 16 ነጥብ 8 በመቶ በ2012 መጨረሻ ወደ 11 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ እንደሚል ትንበያው ያሳያል፡፡

ታዲያ በዕቅዱ ዘመን በቁጠባና በኢንቨስትመንት መካከል ያለውን ሚዛን ለማጥበብ የሚከናወኑ ተግባራት ቢኖሩም ክፍተቶቹን ሙሉ በሙሉ መድፈን ይቻላል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ስለሆነም ጉድለቶቹን ለመሸፈንና የታቀደውን ፈጣን ዕድገት ለማስቀጠል እንዲቻል የውጪ ብድርና ዕርዳታ ማግኘት የግድ ይመስለኛል። ሆኖም ከመንግስት ቀደም ያሉ ተግባራቶች መረዳት እንደሚቻለው አገሪቷ ለዕዳ ጫና ተጋልጣ ዕድገትዋ እንዳይገታ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉ የሚቀር አይመስለኝም። ለነገሩ እስካሁን ድረስ የአገሪቱ የዕዳ ጫና ሁኔታ የቅርብ ክትትል እየተደረገበት የመጣ ነው። እናም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተያዘው የኢንቨስትመንትና የቁጠባ ትልሞችን ከግብ ለማድረስ ከላይ በመረጃ አስደግፌ የገለፅኳቸውን የውጤታማነት እሳቤዎችንና የተግዳሮቶች መፍትሔዎችን በየደረጃው ተግባራዊ ማድረግ ይገባል። የትኛውም ዕቅድ ሊሳካ የሚችለው በተግባሪው ህዝብ ብርቱ ርብርብ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አዎንታዊ ሚና መጫወት ይኖርበታል። ሁላችንም ለዕቅዱ ከተረባረብን ውጤት ማምጣታችን አይቀርም።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy