NEWS

የትግራይ ክልል ለ1 ሺህ 421 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

By Admin

June 22, 2017

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለ1 ሺህ 421 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

ክልሉ ለህግ ታራሚዎቹ ይቅርታ ያደረገው፥ በክልሉ እየተከበረ ያለውን 29ኛ ዓመት የትግራይ ሰማዕታት ቀን ምክንያት በማድረግ ነው፡፡

የክልሉ የማረሚያ ቤቶች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ወልዳይ አብርሃ እንደገለፁት፥ የህግ ታራሚዎቹ ይቅርታ የተደረገላቸው መመዘኛውን አሟልተው በመገኘታቸው ነው።

ይቅርታው በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በአራጣ ብድር፣ ኮንትሮባንድ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የተደራጀ ስርቆትና ሌሎች ከባድ ወንጀሎችን ፈፅመው የተከሰሱ የህግ ታራሚዎችን አያካትትም።

ምንጭ፡-ኢዜአ