#የበለጸገች_ኢትዮጵያ
የሁለተኛው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ የመንገድ ዘርፍ ልማት መርሀ ግብር ውስጥ የተካተተው የአዲስ አበባ _ሞያሌ_ናይሮቢ_ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ _ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ኮንትራት አንድ እና ሁለት መንገዶች ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኮምንኬሽን ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።
የሞጆ_ሓዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ኮንትራት 1 ከሞጆ_መቂ ሲሆን 56.4 ኪሎሜትር የሚሸፍን እና በ3,669,604,000 ብር ወጪ ግንባታው በመከናወን ላይ ነው። ይህ የሞጆ_መቂ አስፋልት ኮንክሪት ስራ በህዳር 2008 ዓ/ም ሬልዌይ ሰባተኛ ግሩፕ በተባለ የቻይና አለም አቀፍ የስራ ተቋራጭ የተጀመረ ሲሆን ኤልኢኤ ኢንተርናሽናል ሊሚትድ ካናዳ እና ኤልኢኢ አሶሴትድ ሳውዝ ኤስያ ፕራይቬት ሊሚትድ(LASA)ከዩናይትድ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነር ፒኤልሲ (UNICONE ) ጋር በመሆን የዚህን መንገድግንባታ የማማከር እና የቁጥጥር ስራውን ያከናውናሉ።
የሞጆ_ሓዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 27%የደረሰ ሲሆን ትልልቅ የድልድይ ግንባታ ፣ማሳለጫ እና ማቋረጫ ፣የአቃፊ ግንብ፣የመንገድ ዳር ትራፊክ ምልክቶችን ያካተተ እና ከአዲስ አበባ _አዳማ የፍጥነት መንድገ ጋር የሚያስተሳስር መንገድ ጨምሮ የተለያዩ አገናኝ መንገዶችን ግንባታ ጨምሮ የያዘ ነው። የዚህ መንገድ ሁለት የሆነው የመቂ_ዝዋይ የፍጥነት መንገድ ግንባታም ዴዎ ኢንጅነሪንግ እና ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ሊሚትድ በተባለ ድርጅት ግንባታ በመፋጠን ላይ ሲሆን ኪንግዶንግ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ ፣ኩንህዋ ኢንጅነሪንግ እና ኮንሰልቲንግ ኮርፖሬሽን ካምፓኒ ሊሚትድ፣ዶንግ አይ ኤል ኢንጅነሪንግ ፒኤልሲ እና ኮር ኮንሰልቲንግ ፒኤልሲ የማማከር እና የምህንድስና ቁጥጥር ስራውን በጋራ እየሰሩት እንደሆነም ታውቋል።የመቂ_ ዝዋይ የመንገድ ስራ በህዳር 2008ዓ/ም የተጀመረ ሲሆን ግንባታው በ ሶስት አመት ተኩል ግዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን የግንባታ ወጪውም በአፍሪካ ልማት ባንክ ይሸፈናል።
ሌላው የሞጆ _ሀዋሳ። የፍጥነት መንገድ ግንባታ ሲሆን ግንባታው በ አራት ኮንትራት ተከፍሎ የሚካሄድ ነው። የዚህ መንገድ የጎን ስፋት 32 ሜትር ሲሆን 90 ሜትር የመንገድ ወሰን ማስከበር ክልል ያካተተ ነው።የኮንትራት ሞጆ _መቂን ጨምሮ የተቀሩት 3 ክንትራቶች ግንባታ አራት መኪኖችን በአንድ ግዜ አራት መኪናዎችን በግራ እና በቀኝ ለማስተናገድ የሚያስችል ነው። የዚህ ኮንትራት ሶስት የሆነው የዝዋይ_አርሲ ነገሌ መንገድ ግንባታ ሲሆን 60.2 ኪሎሜትር ይሸፍናል።የግንባታ ወጪው 7.49 ቢልየን ብር ሲሆን የብድር ስምምነት ከአለም ባንክ ጋር ተደርጎ የጨረታ ሂደቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
55 ኪ/ሜትር የሚሸፍነው የአርሲ ነገሌ_ሀዋሳ መንገድ ግንባታ ሲሆን ለግንባታ የሚሆነው የብድር ስምምነት ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ጋር በቅርቡእንደሚፈረም እና የጨረታ ሂደቱም በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል። የሞጆ_ሀዋሳ መንገድ 10,000 ኪ/ሜ የሚሸፍነው ታላቁ የምስራቅ አፍሪካ ኮሪደር የካይሮ_ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ትራንስ አፍሪካ ሀይዌይ አካል በመሆኑ የሀገራችንን የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መንገድ ነው።