NEWS

የኢትዮጵያ የውስጥ ሰላም ለቀጣናው አገራት ተርፏል» – ጃክ ጃንኮውስኪ በኢትዮጵያ የፖላንድ አምባሳደር

By Admin

June 08, 2017

የኢትዮጵያ የውስጥ ሰላም በቀጣናው ላሉ አገራትም ተርፏል ሲሉ በኢትዮጵያ የፖላንድ አምባሳደር ተናገሩ፡፡

አምባሳደሩ ጃክ ጃንኮውስኪ ሰሞኑን ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ላይ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የውስጥ ሰላሟን በማረጋገጧና በቀጣናው ላይ ትልቅ አገር በመሆኗ ጭምር ለአካባቢው አገራት የሚተርፉ ሥራዎችን ማከናወን ችላለች፡፡

እንደ አምባሳደሩ ገለጻም፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ኃላፊነት አለባት። የኢትዮጵያ መንግሥትም ይሄንን በመረዳት ትልቅ ቁርጠኝነት የሚጠይቁ ተግባራትን እያከናወነ ነው። ወታደሮቹን ወደ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ልኮ አገራቱን ለማረጋጋት እየሞከረ ነው።

«መንግሥት በአገር ውስጥ ያለውን ሰላሙንና ፀጥታውን በቀጣናው ላሉ አገራት እየላከ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው። ይሄ ትልቅ ሥራ ነው። ለቀጣናው አገራትም ትልቅ አስተዋፅኦ ነው።» ብለዋል አምባሳደር ጃክ ጃንኮውስኪ።