NEWS

የ10 ክፍል ሀገር አቀፈ ፈተና በሰላምና ያለምንም ችግር ተጠናቀቀ

By Admin

June 02, 2017

የ10 ክፍል ሀገር አቀፈ ፈተና በሰላም እና ያለምንም ችግር  መጠናቀቁን የሀገር አቀፍ  ፈታናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

ሀገር አቀፍ ፈተናውንም  ከ1 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በሰላም ወስደዋል።

ፈተናዎቹ መሰጠት ከጀመሩበት እስከሚጠናቀቁበት ቀን በፈተና ጣቢያዎቹ ምንም አይነት ችግር አለማጋጠሙን የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት እና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ረዲ ሽፋ ለፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናም ከፊታችን ሰኞ እስከ ሀሙስ የሚሰጥ ይሆናል።

ለሀገር አቀፍ ፈተናውም 288 ሺህ 626 ተማሪዎች ይቀርባሉ ።