Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ድርቅ ወደ ረሃብ እንዳይቀየር ያደረገ አገራዊ አቅም

0 410

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ድርቅ ወደ ረሃብ እንዳይቀየር ያደረገ አገራዊ አቅም

                                                            ደስታ ኃይሉ

የድርቅ አደጋ ለሀገራችን አዲስ ክስተት አይደለም። በተፈጥሮ የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በአመዛኙ የምስራቅ አፍሪካ ህዝቦች በዚህ አደጋ ይጠቃሉ። ከሀገራችን አኳያ ባለፉት ስርዓቶች በንጉሱም ይሁን በአምባገነናዊው የደርግ ስርዓቶች ወቅት ድርቅ ወደ ረሃብነት ተቀይሮ የአያሌ ወገኖቻችንን ህየወት ቀጥፏል። ሀገራችንም በመዝገበ ቃላት ጭምር የድርቅ ተጠቂ ስትደረግ መቆየቷ ይታወሳል።

ይሁንና አዲሲቷ ኢትዮጵያ በአዲስ የልማት አስተሳሰብ መመራት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ድርቅ ቢፈጠርም ረሃብ ግን ሊከሰት አልቻለም። ለዚህ ሁት ጉዳዩችን ማንሳት ይቻላል። አንደኛው የአገራችን ህዝቦች የመረዳዳት ባህል ያለቸው መሆኑንና መንግስት ላለፉት 26 ዓመታት ድርቅ ወደ ረሃብነት እንዳይቀየር በመስራቱ ነው።

ትናንት ቢሆን ኖሮ እንኳን እንዲህ ያለ ድርቅ ተከስቶ ይቅርና በትንንሽ የድርቅ ሁኔታም ስንጠቃ እንኳን አገራችን በየጊዜው ለዓለም አቀፍ  እርዳታ  ተጋላጭ ነበረች። ይሁንና ይህ አካሄድ አሁን ላይ ተሰብሯል። በአዲሲቷ  ኢትዮጵያ ድርቅ ቢከሰትም ወደ ረሃብነት ግን መለወጥ አይችልም። በድርቅ ምክንያት ዜጎች ህይወታቸውን አያጡም። ይህ ሁኔታ የተፈጠረው በተዓምር ሳይሆን መንግስትና ህዝብ ተቀራርበው መስራት በመቻላቸው ነው። በተለይም ኢትዮጰያ ባለፉት 15 ዓመታት ተከታታይና ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ በመቻሏ ድርቁን መቋቋም ችላለች።

እንደሚታወቀው ሁሉ በአየር መዛባት ክስተት ሳቢያ በ50 ዓመት ታሪካችን ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሚሊዩኖች ለድርቅ አደጋ ተጋልጠው በነበረበት ወቅት መንግስት የአንድ ነጥብ አራት ቢሊዩን ዶላር ድጋፍ ለጋሽ ሀገራትን ጠይቆ እንደነበር እናስታውሳለን። ሆኖም ከለጋሾቹ የተገኘው ድጋፍ ይህን ያህል ባለመሆኑ፤ መንግስት በራሱ አቅም ዜጎቹን ለመታደግ ችሏል። ይህም እዚህ ሀገር ውሰጥ ላለፉት ጊዜያት ሰሰሩ በመጡት ልማታዊ ተግባራት የተፈጠረውን አቅም የሚያሳይ ክስተት ሆኖ አልፏል።

በአሁኑ ወቅትም ለድርቅ አደጋ የተጋለጡ ዜጎችን ለመታደግ መንግስት ማናቸውንም ተግባራት ያከናውናል፤ በማከናወን ላይም ይገኛል። መንግስት የችግሩን ስፋትና ጥልቀት አስቀድሞ በመገንዘብ የተፈጠረውን ሁኔታ ለመቋቋም በዜጎችና በኢኮኖሚው  ላይ ሊደርስ የሚችለውን  ጉዳት ለማስቀረት የሚያስችል አቅጣጫ ቀይሶ ተግባራዊ እያደረገ ነው።

እርግጥ በተፈጥሮ የአየር መዛባት ምክንያት በሀገራችን የድርቅ አደጋ ሲከሰት አዲስ ነገር አይደለም። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰት ጉዳይ በመሆኑ ምንም ማድረግ አይቻልም። ሆኖም ይህ በየጊዜው ሀገራችንን የሚጎበኛት የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብነት እንዳይቀየር መንግስት ብርቱ ጥረት አድርጓል።

እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት የመንግስት ትኩረት ምንም ዓይነት የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅ  ቢያጋጥምም፤ ህዝባችን  የማይራብበት ሁኔታን በመፍጠር ላይ ሲረባረብ ቆመቆየቱ አይዘነጋም። የኤልኒኖ አደጋ በተከሰተበት ወቅትም አደጋውን በመቀልበስ የልማት አጋር ሀገራትን ድጋፍ እምብዛም ሳያገኝ ችግሩ ወደ ረሃብነት ሳይቀየር መቋቋሙ ይህን ጥረቱን አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ከማንም የተሰወረ ጉዳይ አይመስለኝም።

በእኔ እምነት መንግስት ከአጭር ጊዜ አኳያ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል በፍጥነት በመድረስና ዕርዳታ ማድረግ እንዲሁም ድጋፉ ልማታዊ  በሆነ አኳሃን ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረጉ ለዜጎቹ ያለውን የኃላፊነትና የተጠያቂነት መንፈስ ስሜትንና ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ነው።

እርግጥ እንኳንስ አሁን የሀገራችንን የአደጋ ተጋላጭነት አቅምን በማጎልበት ላይ በሚገኘው የልማት ስትራቴጂ ምክንያት ከፍተኛ ዕድገት እየተመዘገበና በድርቅ ነባራዊ ማዕቀፍ ውስጥ ሆነን ረሃብ እንዳይፈጠር ማድረግ በተቻለበት በአሁኑ ወቅት ቀርቶ፤ የኢፌዴሪ መንግስት የዛሬ ስምንት ዓመት ገደማ 14 ነጥብ 5 ሚሊዮን ያህል ህዝብ ለምግብ እጥረት በተዳረገበት ወቅት ድርቁ ወደ ረሃብ እንዳይሸጋገር ብርቱ ጥረት አድርጎ ተሳክቶለት እንደነበር የምንዘነጋው እውነት አይደለም።

ይህ ሁኔታ ደግሞ ዝም ብሎ የተፈጠረ ሊሆን እንደማይችል ከማንም የተሰወረ ሊሆን የሚችል አይመስለኝም— መንግስት ቀደም ባሉት ጊዜያት የአርሶና የአርብቶ አደሩን ህይወት ለመለወጥ ካከናወናቸው ተገቢ ተግባራት የመነጨ እንጂ። እርግጥም የኢፌዴሪ መንግስት የአርሶና የአርብቶ አደሩ ኑሮ እንዲሻሻል ተገቢውን ትኩረት ሰጥቷል። በዚህም አርሶ አደሩ ከራሱ ተርፎ ለገበያ በማምረት ተጠቃሚ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ፣ ሀገሪቱም ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ጎዳና እንዲፈጠር አድርጓል። ለዚህ ስኬት በመንግስት በኩል የተወሰዱት እርምጃዎች በቂ ማሳያዎች ናቸው ማለት ይቻላል።

እንደሚታወቀው ሁሉ ኢትዮጵያ ለእርሻ የሚውል ሰፊ መሬት አላት። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች በአርሶ አደሩ እጅ እንዳለ የሚታሰበው መሬት አነስተኛ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ካለችውም መሬት ቢሆን የሚያገኘው ምርት ዝቅተኛ ነው። አመራረቱም እጅግ ኋላ ቀር ሆኖ ቆይቷል።

ይህን ዕውነታ የተገነዘበው የኢፌዴሪ መንግስት ዘርፈ ብዙ የማሻሻል ጥረቶች አድርጓል። በውጤቱም አነስተኛ ይዞታ ባላቸው አነስተኛ የአርሶ አደሮችን ማሳ ላይ ለውጥ ማምጣት አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ ሰብሯል። አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ትኩረት ከመስጠት ይልቅ ለሰፋፊ እርሻዎች ትኩረት መስጠትና ለውጥ ማምጣትን የሚሰብኩ ወገኖችን አፍ ማስያዝ የቻለ ትክክለኛ መስመርን በመከተል ውጤት ማምጣት ችሏል።

በአርብቶ አደሩም አካባቢ ተመሳሳይ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በመቅረፅና ቀደ ተግባር እንዲገባ በማድረግ ድርቅ ሊፈጥር የሚችለውን አደጋ በአያሌው መቀነስ ተችሏል። ከእነዚህ መንግስታዊ ጥረቶች ውስጥ የአርብቶ አደር የልማት ፓኬጆችን በመቅረፅ፤ አርብቶ አደሩ ከልማዳዊ የአኗኗር ባህል ወጥቶ ወደ ዘመናዊ ህይወት እንዲቀየር፣ ከአርብቶ አደሩ ጋር በመነጋገር ድርቅን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችሉ የመስኖ ልማት ስራዎችን በማስፋፋት ወደ ከፊል አርሶ አደርነት እንዲሸጋገር ብሎም ምርጥ ዝርያዎችን አግኝቶ ተጠቃሚነቱን እንዲያሳድግ፣ የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውሃዎችን በአግባቡ የማሰባሰብ ስራዎችን እንዲያጠናክር፣ የመሰረተ ልማትና የሌሎች የልማት ዘርፎች ተቃሚ ይሆን ዘንድ በፍፁም ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የሰፈራ ፕሮግራምን እንዲቀበል፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲጠናከርና በዚህም ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር የማድረግ ስራዎችን ማከናወኑና በማከናወን ላይ መሆኑ ጥቂት ተጠቃሽ ምሳሌዎች ናቸው።

ባለፉት ዓመታት የመንግስት ትኩረት ምንም ዓይነት  የአየር ንብረት  መዛባትና ድርቅ ቢያጋጥምም፤ ህዝባችን የማይራብበት ሁኔታን በመፍጠር ላይ ሲረባረብ ቆይቷል። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ መንግስት ከአጭር ጊዜ አኳያ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰተውን ድርቅ ለመከላከል በፍጥነት በመድረስና ዕርዳታ ማድረጉ  እንዲሁም ድጋፉ ልማታዊ በሆነ አኳኋን ጥቅም ላይ እንዲውል የክትትል አሰራርን መከተሉ አሁን ላለበት አቅም አብቅተውታል። ነገም ቢሆን ይህ አቅም እየጎለበተ የሚሄድ በመሆኑ መንግስት የህዝቡን ድጋፍ ይዞ የሚመጣን ችግር መቋቋም ይችላል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy