Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

320 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ሆኖ የተዘጋጀው የፌደራል መንግስት የ2010 ረቂቅ በጀት ለምክር ቤቱ ቀረበ

1 826

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢፌዴሪ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም ተከስተ የ2010 የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አቅርበዋል።

ረቂቅ በጀቱም 320 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ሆኖ ነው የተዘጋጀው።

ከአጠቃላይ የመደበኛ እና ካፒታል የመንግስት ወጪ በጀት ውስጥ 61 ነጥብ 8 በመቶ ያህሉ ቅድሚያ ትኩረት ለተሰጣቸው የትምህርት፣ የመንገድ፣ የግብርና፣ የውሃና የተፈጥሮ ሃብት፣ የጤና እና የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራሞች የሚውል ነው።

በተጨማሪም ለወጣቶች የተዘዋዋዋሪ ፈንድ፣ ለከተማ ልማትና ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ከፍ ያለ በጀት ተይዟል።

ረቂቅ በጀቱ ከ2009 በጀት ዓመት መጀመሪያ ከጸደቀው በጀት ጋር ሲነጻጸር የ46 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወይም የ16 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ባቀረቡት እቅድ ጠቅሰዋል።

የቀጣይ ዓመቱ በጀት በ2009 በጀት ዓመት የጸደቀውን የተጨማሪ በጀት ጨምሮ ከተስተካከለው 292 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የወጪ በጀት አንጻር የ28 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ልዩነት ነው ያለው።

ከ2010 በጀት ውስጥ 114 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ለካፒታል፣ 81 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 7 ቢሊየን ብር ለዘላቂ ልማት እና 117 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለክልሎች ድጋፍ ተመድቧል።

ከጠቅላላ በጀቱ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው ለክልሎች የሚደረግ ድጎማ የተያዘው ሲሆን፥ ይህም የ36 ነጥብ 6 በመቶ ድርሻ አለው።

ክልሎች በርካታ የልማት ስራዎችን ስለሚሰሩና ወጪው በዚያው ልክ በመሆኑ ከፍተኛ የድጋፍ በጀት እንደተመደበላቸው ዶክተር አብርሃም ተናግረዋል።

እንዲሁም የክልሎችን የዘላቂ ልማት ግቦችን የሚያጠናክር 7 ቢሊየን ብር በ2010 የፌደራል መንግስት በጀት ውስጥ እንዲካተት መደረጉን ነው የገለፁት።

በጀቱ በዋናነት የአግሮ ኢንዱስትሪዎችን ለመገንባት፣ ለማምረቻ ኢንዱስትሪዎች እና ለስራ እድል ፈጠራ ፕሮግራሞች ለማዋል የታቀደ ነው።

የካፒታል በጀት ከአጠቃላይ በጀቱ ባለው ድርሻ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ 35 ነጥብ 7 በመቶ ያህል ድርሻ አለው።

ለመደበኛ ወጪ የተያዘው በጀት ደግሞ ከ2009 ጋር ሲነጻጸር የ1 ነጥብ 4 በመቶ ብላጭ ነው ያለው።

የፌደራል መንግስትን የካፒታል ወጪዎች ለመሸፈን የታቀደው ከሀገር ውስጥ ከሚሰበሰብ ገቢና ከውጭ ሀገር በሚገኝ እርዳታና ብድር ነው።

ከመንግስት የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ፣ ከእርዳታና ከብድር የሚገኘው ገቢ በቅደም ተከትል 80 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር፣ 14 ነጥብ 3 ቢለየን ብር እና 20 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ነው።

በመሆኑም በጀቱ ዘላቂ ልማትን በማምጣት ድህነትን ለማስወገድ ቁልፍ ሚና ባለቸው ክፍላተ ኢኮኖሚዎች የመሰረተ ልማት አውታሮችን በማስፋፋት የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽንን በማረጋጋጥ ላይ ያመዘነ መሆኑ በበጀት ረቂቁ ላይ ቀርቧል።

ለመደበኛ፣ ለካፒታል እና ለብሔራዊ ክልል መንግስታት የበጀት ድጋፍ እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማጠናከሪያ ወጪ በአጠቃለይ 320 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት ቀርቧል።

በታቀደው የፌደራል ገቢ እና በቀረበው የወጪ በጀት መካከል የ53 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ጉድለት አለ።

የበጀት ጉድለቱን በሀገር ውስጥ በሚገኝ በጀት ለመሸፈን የታቀደ ሲሆን፥ የሀገር ውስጥ የብድር መጠኑ ከአጠቃላይ የሀገር ውስት ምርት /ጂዲፒ/ አንጻር 2 ነጥብ 5 በመቶ ነው።

ይህም የማይክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ተግባራዊ ከተደረገው የገንዘብ ፖሊስ ጋር ተመጣጣኝ በመሆኑ በዋጋ ንረት ላይ ተፅዕኖ አያሳርፍም ብለዋል።

የፋይናንስ ውስንነትን፣ የወጪ ንግድ መዳከምን ለማስተካከል እና የበጀቱን ተፈጻሚነት እውን ለማድረግ ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባው አሳስበዋል።

የ2010 ረቂቅ በጀት ሲዘጋጅ በበጀት ዓመቱ የሚካሄዱ ማህበራዊ ኢኮኖሚዊ የልማት ስራዎችን፣ የዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የኢኮኖሚ ሁኔታን በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረውን አንድምታ፣ የበለፀጉት ሀገራት ለታዳጊ ሀገራት የሚሰጡት ብድር እና እርዳታ ሊቀንስ እንደሚችል ተሳቢ ተደር የተዘጋጀ ነው፡፡

የ2010 የወጪ በጀት ሲዘጋጅ አማካይ የዋጋ እድገቱ ከ8 በመቶ እንደማያድግ፣ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ የምርት በጊዜው የገበያ ዋጋ በ2010 የ19 ነጥብ 1 በመቶ እድገት እንደሚኖረው፣ የገቢ እቃዎች ዋጋ የ12 ነጥብ 5 በመቶ እድገት እንደሚኖረው ታሳቢ መደረጉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት በ2010 በ11 ነጥብ 1 በመቶ እንደሚያድግ ግምት ተሰጥቷል።

ምክር ቤቱም ለዝርዝር እይታ ረቂቅ በጀቱን ለበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። FBC

  1. ሠላም በላይ says

    በየክልሉ ያሉት አስፈጻምወች በደል እያደረሱ ነው ።የሥራ ተቀጣርዎችን በምናይበት ጊዜ በብር ነው ።ደግሞም የምወጣው ማስተወቅያ የዘመዶቻቸውን መሥፈርት የምጠቅስ እንጅ በጭራሽ የማይታመን ነገር ነው እየተደረገ ያለው በክልሎች ፡፡እኔ በለሁበት ክልል በብርና በዘመድ ብቻ ነው ስራ ምገኘው ፡፡ከዝህም የተነሣ እኔ ከተመረኩ እስከዛሬ ለአረት አመት ስራ አጥ ነኝ ፧፧ደግሞም በባጄታችሁ አልደነቅም

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy